ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ የተገነባው ናሁሰናይ ሆቴል የፊታችን ቅዳሜ ይመረቃል፡፡

ናሁሰናይ ሆቴል ቅዳሜ የካቲት 23/2016 ዓ.ም እንደሚመረቅ ተነግሯል፡፡

በደብረማርቆስ በንግድ ስራ ቢዝነስ የጀመሩት የሆቴሉ ባለቤት አቶ እሱባለው ናሁሰናይ፣ የምግብ ዘይት ማምረት ላይ ተሰማርተው ከ10 አመት በላይ ከሰሩ በኋላ አሁን እህት ድርጅት የሆነው ናሁሰናይ ሆቴል በአዲስ አበባ አዲሱ ገበያ ሸገር መናፈሻ አከባቢ ገንብተው አጠናቀዋል።

ሶስት አመት የግንባታ ጊዜ የወሰደው ሆቴሉ ከ70 እስከ 100 ዜጎች የስራ እድል እንደፈጠረ የሆቴሉ ስራ አስኪያጅ አቶ መላኩ ካሳሁን ተናግረዋል።

ናሁሰናይ ሆቴል 46 የተለያዩ የመኝታ ክፍሎች ያሉት ሲሆን፣ 5 የራሳቸው ማብሰያ ያላቸው መኝታ ክፍሎች፣ 5 ትዊን መኝታ ያላቸው ክፍሎች፣ 26 ስታንዳርድ የመኝታ ክፍሎች እንዳሉት ተነግሯል።

400 ካሬ ላይ ያረፈው ናሁሰናይ ሆቴል ከሁለት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ እንደፈጀ አቶ መላኩ ገልጸዋል።
የመኝታ፣ የምግብ እና መጠጥ፣ ስፓ ጂም፣ 2 ባር እና 200 እንግዶች ማስተናገድ የሚችል የመሰብሰቢያ አዳራሽ ሆቴሉ አካቶ እንደያዘም ተገልጿል።

ባለሃብቱ በቀጣይም ሌሎች ሆቴሎችን የመገንባት እቅድ እንዳላቸውም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ሆቴሉ የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 23/2016 ዓ.ም የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት እንደሚመረቅ በዛሬው እልት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተነግሯል፡፡

በልዑል ወልዴ
የካቲት 21 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply