ከ2014 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የማለፊያ ውጤት ይፋ ሆኗል።
ኩረጃን ለማስቀረትና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በሚል፣ በልዩ ሁኔታ ከተሰጠው የ2014 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ የመልቀቂያ
ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርስቲ በተሰጠው ፈተና ከ980 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል።
የፈተና ውጤቱ ከዛሬ እኩለ ሌሊት ጀምሮ በበይነመረብ ይፋ እንደሚደረግ፣ ተማሪዎችም በተሰጣቸው የመለያ ቁጥር ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ታውቋል።
በዚህም ተፈታኞች ከዛሬ ሌሊቱ 5 ሰዓት ከ30 ጀምሮ በ በዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ፤ በ6284 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝግባ ቁጥራቸውን (Registration Number) ብቻ በመላክ ወይም በቴሌግራም https://t.me/eaesbot ማየት የሚችሉ መሆኑን ተገልጿል፡፡