ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያላቸው የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው ምግብና መድሃኒቶች እንዲወገዱ መደረጉ ተገለጸ፡፡በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ስድስት ወራት ከ22 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር…

ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያላቸው የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው ምግብና መድሃኒቶች እንዲወገዱ መደረጉ ተገለጸ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ስድስት ወራት ከ22 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸውና የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው ምግብ፣ መድሃኒቶችና የመጠጥ ምርቶች መወገዳቸውን የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታውቋል።

የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አሰፋ ተሬሳ እንደገለጹት፣ ባለፉት ስድስት ወራት በመደበኛና በድንገተኛ በተካሄዱ የቁጥጥር ሥራዎች በጤና ላይ ጉዳት የሚያደረሱ ምግቦችን ማስወገድ ተችሏል።

እነዚህም የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸውና ግምታቸው ከ22 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ ምግቦች፣ መድሃኒቶችና መጠጦች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

የመጠቀሚያ ጊዚያቸው አልፎ ከተወገዱት መካካል ከ45 ሺህ ሊትር በላይ መጠጦችና ከ13 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ የምግብ ምርቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።

እነዚህ ምርቶች ከ13 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ መሆኑንም አቶ አሰፋ ጨምረው አስታውቀዋል።

ባለሥልጣኑ ግኝቱን መሠረት አድርጎ በ695 ተቋማት የጽሑፍ ማስጠንቀቂያና በ169 ተቋማት ላይ ደግሞ የማሸግ እርምጃ ወስዷል ነው ያሉት።

በልዑል ወልዴ

ጥር 03 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8

Source: Link to the Post

Leave a Reply