“ከ274 ሺህ በላይ የትግራይ ሠራዊት አባላት ትጥቅ ይፈታሉ” – ብሔራዊ የተሐድሶ ኮሚሽን

የትግራይ ኃይል አባላትን ትጥቅ ለማስፈታት፣ ለማሰናበትና ከማህበረሰቡ ጋር ዳግም እንዲቀላቀሉ የሚያስችል የቅድመ ትግበራ ውይይት በመቀለ ተካሂዷል።

በዚህ ሳምንት መጀመርያ ላይ በተካሄደው ምክክር ላይ የፌደራል መንግሥት ተወካዮች፣ የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት አመራሮች እና የአፍሪካ ኅብረት የስምምነት ክትትል፣ አረጋጋጭ እና አስከባሪ ኮሚቴ አባላት መገኘታቸውን የብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ተመስገን ጥላሁን በኤክስ ገጻቸው አስታውቀዋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንቶች እንዲሁም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በዚህ ምክክር ላይ የትግራይ ተዋጊዎችን በመበተን እና ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ወደ ኅብረተሰቡ የማዋሃድ ፕሮግራም፣ ፕሮጀክቶች መንደፍ እንዲሁም የመጀመሪያው የትግበራ እቅድ ላይ ውይይት እንደሚደረግ ተጠቅሶ ነበር።

ግንቦት 09 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply