ከ3 ሺሕ 700 በላይ ተጠርጣሪዎች የፍርድ ሂደት

ከ3 ሺሕ 700 በላይ ሰዎች የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በተቀሰቀሰው አመፅ ተጠርጥረው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ነው፡፡በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የድንብር ተሸጋሪ ወንጀሎች ክትትል ዳይሬክተሩ ተመስገን ላጲሶ ናቸው ይህን ለአሐዱ ቴሌቪዥን የተናገሩት፡፡

የፕሬስ ሰክሪታሪያት ኃላፊው አወል ሱልጣን በበኩላቸው በደረሰው የንብረት ውድመትና የዜጎች ህይወት ማለፍ የሚጠረጠሩ ሰዎችን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል፡፡ተጠርጣሪዎቹ የተፋጠነ ፍትሕ እንዲያገኙ ከማድረግ አንፃር አቃቤ ሕግ ነገሮችን እንዲዘገዩ በማድረግ ሲወቀስ ይሰማል፡፡

የፕሬስ ሰክሪታሪያት ኃላፊው ግን ዐቃቤ ሕግ የፍርድ ሂደቱ የተፋጠነ እንዲሆን እየሰራ መሆኑንና ወደ መከላከያ ምስክር ማሰማት ደረጃ ላይ መደረሱን ገልፀዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብቶች ኮሚሽን ከወር በፊት ባወጣው ሪፖርት የድምፃዊውን መገደል ተከትሎ በተከሰቱ ሁከቶች እና የቡድን ጥቃቶች በትንሹ 123 ሰዎች መገደላቸውን በመግለፅ መንግሥት ተጠያቂዎችን ሁሉ ሕግ ፊት እንዲያቀርብ መጠየቁ ይታወሳል።

አሐዱ ቴሌቪዥን

The post ከ3 ሺሕ 700 በላይ ተጠርጣሪዎች የፍርድ ሂደት appeared first on አሐዱ ቲቪ እና ራድዮ 94.3.

Source: Link to the Post

Leave a Reply