You are currently viewing ከ3 ወራት በላይ ልዩ ወታደራዊ ስልጠና የወሰዱ ኮማንዶዎችን በራያ ቆቦ ከተማ ማስመረቁን የምስራቅ አማራ ፋኖ አስታውቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   መጋቢት 24 ቀን 2014 ዓ.ም…

ከ3 ወራት በላይ ልዩ ወታደራዊ ስልጠና የወሰዱ ኮማንዶዎችን በራያ ቆቦ ከተማ ማስመረቁን የምስራቅ አማራ ፋኖ አስታውቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 24 ቀን 2014 ዓ.ም…

ከ3 ወራት በላይ ልዩ ወታደራዊ ስልጠና የወሰዱ ኮማንዶዎችን በራያ ቆቦ ከተማ ማስመረቁን የምስራቅ አማራ ፋኖ አስታውቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 24 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ መጋቢት 21 ቀን 2014 በሰሜን ወሎ ዞን ኡርጌሳ ላይ ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ ፋኖዎችን በድምቀት ያስመረቀው የምስራቅ አማራ ፋኖ በተመሳሳይ መጋቢት 22/2014 በደቡብ ወሎ ዞን የሐይቅ ፋኖ አባላቱን ማስመረቁን አሚማ መዘገቡ ይታወሳል። በተያያዘ በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ ከ3 ወራት በላይ ልዩ ወታደራዊ ስልጠና እንዲሰለጥኑ የተደረጉ በርካታ ኮማንዶዎችን መጋቢት 24/2014 በድምቀት ማስመረቁን አስታውቋል። ከአሚማ ጋር ቆይታ ያደረጉት የምስራቅ አማራ ፋኖ የሰው ኃይል አስተዳደሩ ፋኖ አስፋቸው ሲሳይ እንደገለጹት ለወራት ከሰለጠኑት አባላቱ መካከል በመለየት ነው ከ3 ወራት በላይ አሰልጥነው በድምቀት ያስመረቁት።

Source: Link to the Post

Leave a Reply