ከ30 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ

ከ30 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 17 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ከ30 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ መያዙ ተገለጸ።

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ÷ በአምስት የተለያዩ መጋዘኞች ውስጥ ተከማችተው የተገኙ 30 ሚሊየን 174 ሺህ 255 ብር ግምት ያላቸው የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በህብረተሰቡ ጥቆማ መያዛቸውን አስታውቀዋል።

በምስራቅ ሃረርጌ ሜኢሶ ወረዳና አሰቦት ከተማ ውስጥ በአምስት ትላልቅ መጋዘኖች ያለአግባብ ተከማችተው የነበሩ የኮንትሮባድ እቃዎች በአዋሽ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሰራተኞች፣ በኦሮሚያ ልዩ ኃይልና በህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥረት መያዛቸውን ጠቁመዋል።

ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች ውስጥ መዳኃኒቶች፣ ምግብ ነክ ምርቶች፣ የሲጋራዎች፣ አደንዛዥ ዕፆች እና አዳዲስና ልባሽ ጨርቆችን ጨምሮ ሌሎች ንብረቶች ተይዘው ወደ ጉምሩክ መጋዘን ገቢ መደረጋቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

The post ከ30 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply