
በሳዑዲ አረቢያ ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ናቸው የተባሉ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውን ስደተኞች በተጨናነቁ እስር ቤቶች በሰቆቃ ውስጥ እንደሚገኙ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ። ዓለም አቀፉ ሰብአዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሳዑዲ አረቢያ እስር ቤቶች ውስጥ ያሉበትን ሁኔታ እና እየገጠማቸው ያለውን አሳሳቢ ሁኔታን በተመለከተ ባወጣው መግለጫቁጥራቸው ከ30 ሺህ እንደሚልቅ አመልክቷል።
Source: Link to the Post