ከ35 በላይ አመራሮች እና ባለሙያዎች በመሬት ወረራ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ከ35 በላይ የሚሆኑ ባለሙያዎች እንዲሁም 11 በላይ አመራሮች በ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/BpvzAiPdJhAZ5uHDHjHzlFyGaBrMtM3bYyax2WRyRJ8n_nv3tgc2wblmy8tcdMBxQMcHvT3VbFM4722ihVxendTxefgcGYtGk8YEjDY4u00AFGcQW_iboAKyWHEofCWqkyYTY1jNmplVISURqjyZesPYjyc7axmziU5_6s5V64eWqTRTQFIVaJldUNTlgweNUT6QxcEq46VqABLIUNGmawAbJ5Xy8N5yV66s7tMFxLtZATnJfhXNFbLStxbjPO7HthFt5jNWNcbPVmcRDJaFCTG5Vi8ODTwUv8kO2oRDmd1bbB7O4A3k4BwEQp-pAf0hcCTSXfPIuhEJx4aDspugzQ.jpg

ከ35 በላይ አመራሮች እና ባለሙያዎች በመሬት ወረራ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ከ35 በላይ የሚሆኑ ባለሙያዎች እንዲሁም 11 በላይ አመራሮች በህገ-ውጥ የመሬት ወረራ ተሳትፈው መገኘታቸውን አስታውቋል፡፡

ፍትህ ቢሮው ለጠቅላይ አቃቤ ህግ አመራሮችና ባለሙያዎች ላይ መረጃ በማደራጀት መላኩን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ወንጀል መከላከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብዮት ጅፋር ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቁት፣ በዚህ ድርጊት ላይ ከተያዙት ውስጥ አስተዳደራዊ እርምጃ የተወሰደባቸው ሲኖሩ ሌሎች ደግሞ ጉዳያቸው በወንጀል እየተጣራ ያለ እንዲሁም በፍርድ ሂደት ላይ የሚገኙ መኖራቸውን አስታውቀዋል፡፡

እነዚህ አመራሮች እና ባለሙያዎች መሬት ባንክ የገባን መሬት ለግል ጥቅማቸው ለማዋል በማሰብ ከግለሰቦች ጋር በጋራ በመሆን ጥቅም ለማግኘት ሲሰሩ የነበሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

በለሚ ኩራ፣በልደታ እና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ አንድ አንድ አመራሮች እና ባለሙያዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Source: Link to the Post

Leave a Reply