ከ415 ሽህ በላይ ተማሪዎች በአማራ ክልል የ8ተኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና እየወሰዱ ነው፡፡         አሻራ ሚዲያ    ታህሳስ 12 /2013 ዓ.ም ባህር ዳር በኮሮና…

ከ415 ሽህ በላይ ተማሪዎች በአማራ ክልል የ8ተኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና እየወሰዱ ነው፡፡ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 12 /2013 ዓ.ም ባህር ዳር በኮሮና…

ከ415 ሽህ በላይ ተማሪዎች በአማራ ክልል የ8ተኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና እየወሰዱ ነው፡፡ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 12 /2013 ዓ.ም ባህር ዳር በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ክልል አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተና ከዛሬ ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል፡፡ ክልል አቀፍ ፈተናው በ5 ሽህ 162 የፈተና ጣቢያዎች እንደሚሰጥ ከትምህርት ቢሮ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡ የፈተና ቁሳቁሶች ተሟልተው እየተሰጠ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን በተለይ ለአብመድ ገልፀዋል፡፡ፈተናው በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው የፀጥታ ዝግጅት ተደርጎ ወደ ሥራ ተገብቷል ብለዋል፡፡ ፈተናው በሁሉም አካባቢዎች በሰላም መጀመሩ ተገልጿል፡፡ በመደበኛ፣ የማታ እና የግል ተፈታኞችን ጨምሮ ከ415 ሽህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ተመልክቷል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply