ከ5 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ መድሃኒቶችን በማጉደል የተጠረጠረው ግለሰብ ላይ ዐቃቤ ህግ ክስ መሰረተ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ግምታዊ ዋጋቸው ከ5 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ መድሃኒቶችን በማጉደል ለግል ጥቅሙ አውሏል በሚል የተጠረጠረው ግለሰብ ላይ ዓቃቤ ህግ ክስ መመስረቱን አስታወቀ፡፡

ሚካኤል ዘውገ ተሰማ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 31(2) ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ በፈፀመው ከባድ የእምነት ማጉደል የሙስና ወንጀል ክስ ቀርቦበታል፡፡

ተከሳሹ የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ውስጥ የመጋዝን ኃላፊ እንደነበርም ተጠቅሷል፡፡

በመጋዘን ውስጥ በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ ከወጪ ቀሪ ዋጋቸው ውድ የሆኑትን Rho-D ወይም Anti-D የተባለው በደም ውስጥ የሚገኝ RH አንቲጅን አለመጣጣምን በሽታ ለማከም የሚውሉ ብዛታቸው 4 ሺህ 949 መድሐኒቶች ማጉደሉን ዐቃቤ ገልጿል፡፡

ይህን ተከትሎም በፈፀመው ከባድ የእምነት ማጉደል እና የሙስና ወንጀል በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ዐቃቤ ህግ ክስ መመስረቱን ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ከ5 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ መድሃኒቶችን በማጉደል የተጠረጠረው ግለሰብ ላይ ዐቃቤ ህግ ክስ መሰረተ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply