ከ70ዓመት በኋላ የዮኒቨርስቲዎች የባህል ማዕከላት ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ሊካሄድ ነዉ ተባለበአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ በተዘጋጀዉ ፌስቲቫል ላይ የሁሉም ዮኒቨርሲቲዎች ባህል ማዕ…

ከ70ዓመት በኋላ የዮኒቨርስቲዎች የባህል ማዕከላት ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ሊካሄድ ነዉ ተባለ

በአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ በተዘጋጀዉ ፌስቲቫል ላይ የሁሉም ዮኒቨርሲቲዎች ባህል ማዕከላት የሚሳተፉበትና ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚቆይ ነዉ ተብሏል።

ፌስቲቫሉ ዋና አላማው በዮኒቨርስቲዎች መካከል ትስስርን ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን የአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል ዳይሬክተር ረዳት ኘሮፌሰር ተስፈዬ እሸቱ ተናግረዋል።

ከዚህ በኋላም ዮኒቨርሲቲዎች በየተራ ሀላፊነት ወስደው የሚያዘጋጁት አመታዊ ክብረ በዓል ሆኖ እንደሚቀጥል አስረድተዋል፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ የሚከበር “ኢንተርናሽናል ፌስቲቫል” እንዲሆን ለማስቻል ከወዲሁ ታቅዶ እየተሰራበት እንደሚገኝም ተጠቅሷል።

ፌስቲቫሉም ጥር 27 ከቀኑ 11 ሰአት ጀምሮ እንደሚካሄድ ሰምተናል፡፡

በፌስቲቫሉም ሁሉም የሀገሪቱ ማህበረሰቦች አዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ ዋናው ግቢ በመገኘት ከሰኞ እስከ እሮብ ፌስቲቫሉ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ ተገልጿል ።

በሀመረ ፍሬዉ
ጥር 23 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply