ከ8 ሺህ በላይ የሆኑ የብልፅግና ፓርቲ አባላት ተባረዋል ተባለ፡፡

በዘንድሮው የበጀት ዓመት በስድስት ወር የስራ አፈፃፀም ላይ በተደረገ ግምገማ ከ8 ሺህ በላይ የብልፅግና ፓርቲ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ይህን የገለፁት በትላንትናው ዕለት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በነበራቸው ቆይታ ፤ከፓርቲዎች በብልሹ አሰራር ዙሪያ ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡

ከ8 ሺህ በላይ የሚሆኑት የብልፅግና ፓርቲ አባላት እንደ ስራቸው አስተዳደራዊ እርምጃ ከመውሰድ በተጨማሪ እስከ ማባረር የደሰረ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

መጋቢት 2015 ዓ.ም ፓርቲው ባካሄደው ጉባዔ ላይ የፓርቲው ፕሬዝዳንት ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ፤ ፓርቲው በኢትዮጵያ ታሪክ ከዚህ በፊት ከነበሩ ፓርቲዎችና ድርጅቶች በቁጥርም፥ በአደረጃጀትም፥ በሀሳብም የተለየ ፓርቲ መሆኑንም መግለጻቸው የሚታወስ ነው፡፡

በወቅቱ ፓርቲው በመላው ሀገሪቱ ከ11 ሚሊየን በላይ አባላት እንዳው በመግለፅ፤ ሁሉም ብሄሮች በሚገባቸው ልክ የተወከሉበት ፓርቲ መሆኑንም አስታውቀዋል።

ገዢው ፓርቲ ብልፅግና ባለስልጣናት መካከል የክህሎት፣ የመቀራረብና የአስተሳሰብ አንድነት ያመጣል የተባለ ስልጠናና ውይይት በሁሉም ክልሎች ማካሄዱ የሚታወስ ነው፡፡

ልኡል ወልዴ

መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply