ከ80 ሺህ በላይ የሚሆኑ የፍሳሽ ማስወገጃ ጉድጓድ ክዳኖች ስርቆት ተፈጽሟል ተባለ፡፡
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በመዲናዋ ከ80 ሺህ በላይ የሚሆኑ የፍሳሽ ማስወገጃ ጉድጓድ ክዳኖች ስርቆት ተደርጓል ብሏል፡፡
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በመዲናችን አዲስ አበባ ከ80 ሺህ በላይ የፍሳሽ ማስወገጃ ጉድጓድ ክዳኖች መሰረቃቸውን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግሯል፡፡
ከፍተኛ ወጪ ወቶባቸው የተቀመጡ የፍሳሽ ማስወገጃ ጉድጓድ መሸፈኛ ክዳኖች በስርቆት እየጠፉ ነው ሲሉ የከተማዋ የውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን የኮሚኒኬሽ ዳይርክተር ወ/ሮ ሰርካለም ጌታቸው ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
በከተማዋ ከ1 ሺህ 6 መቶ ኪ.ሜ በላይ የተዘረጋ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር እንዳለ የገለጹት ዳይሬክተሯ ፤ከ80 ሺህ በላይ የሚሆኑ ክዳኖች ተሰርቀው ተነስተዋል ብለዋል፡፡
ከዚህም የተነሳ ለፍሳሽ ማስወገጃ ተብለው በተዘጋጁ ጉድጓዶች ውስጥ ደረቅ ቆሻሻዎች ስለሚጣሉ ጉድጓዶቹ ይደፈናሉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ይህም በክረምት ወቅት ከሚዘንበው ከፍተኛ ዝናብ የተነሳ፣ ከከተማው የተለያዩ አከባቢዎች የሚነሱ ፍሳሾች ከጉድጓዱ ውጭ በመሆን የትራፊክ አደጋን ጨምሮ የተለያዩ አደጋዎችን እንደሚያደርሱ ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም የከተማዋ ነዋሪዎችም ሆነ የህግ አካላት ይህንን ወንጀል የመከላከል ስራን በጋር እንደሲሩ ዳይሬክተሯ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በመሳይ ገ/መድህን
ጥቅምት 01 ቀን 2016 ዓ.ም
ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video