ከ80 በላይ ኩባንያዎችን ያሳተፈው የአዲስ ቻምበር ዓለምአቀፍ የእርሻ እና የምግብ ንግድ ትርኢት ተጀምሯል፡፡ከ70 በላይ የሃገር ውስጥ እና ከ15 በላይ የሚሆኑ የውጭ ኩባንያዎችን የሚያሳ…

ከ80 በላይ ኩባንያዎችን ያሳተፈው የአዲስ ቻምበር ዓለምአቀፍ የእርሻ እና የምግብ ንግድ ትርኢት ተጀምሯል፡፡

ከ70 በላይ የሃገር ውስጥ እና ከ15 በላይ የሚሆኑ የውጭ ኩባንያዎችን የሚያሳትፈው 14ተኛው የአዲስ ቻምበር አለምአቀፍ የእርሻ እና የምግብ ንግድ ትርኢት በሚሊኒየም አዳራሽ ተጀምሯል፡፡

ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ የተነገረለት ይህ የንግድ ትርኢት፣ ከተሳታፊ ኩባንያዎች በተጨማሪ በሺህዎች የሚቆጠሩ ጎብኚዎች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የዘንድሮው የንግድ ትርኢት ምቹ የአየር ፀባይ በአላት ኢትዮጵያ የግብርና ምርቶችን ከማምረት ባለፈ፣ በምርት ጥራት በአለምአቀፍ ደረጃ ተመራጭ መሆንን አላማው አድርጎ የተነሳ መሆኑን፣ የአዲስ አበባ ንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ ተናግረዋል፡፡

የንግድ ትርኢቱ ሃገር ውስጥ ያሉ ድርጅቶችን ከአፍሪካ እና ከመካከለኛው ምስራቅ ከመጡ ኩባንያዎች ጋር ጥምረት ለመፍጠር ፋይዳው የጎላ መሆኑን ፕሬዝዳንቷ ተናግረዋል፡፡

ይህም በግብርናው ዘርፍ ያለውን የግንዛቤ ክፍተቶችን በመሙላት፤የአቅርቦት እና የምርት ችግርን በመቅረፍ የምግብ ዋስትናችንን ለማረጋገጥ እንደሚረዳ ወ/ሮ መሰረት ተናግረዋል፡፡

በርካታ የሃገራችን ህዝብ በግብረናው ላይ ህይወቱን የመሰረተ ቢሆንም ፤የጥራት እና የምርት ተደራሽነት ችግር በሚፈለገው ልክ ውጤት እንዳይኖር ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ካለው የጸጥታ ችግር የተነሳ ፤በተፈለገው ልክ ምርቶችን ከቦታ ወደ ቦታ አዘዋውሮ ለመሸጥ አስቸጋሪ ሆኗል ያሉት ፕሬዝዳንቷ፤ይህም ሃገሪቱ ላይ ኑሮ እንዲንር ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን
ህዳር 27 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply