ከ90 ሺ በላይ ዜጎች ከፍልሰት ተመልሰዋል ተባለ፡፡የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስተር ከሳውዲ፣ ከኦማን፣ከየመን እና ከሱዳን ከ90 ሺ በላይ ዜጎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን አስታውቋል፡፡…

ከ90 ሺ በላይ ዜጎች ከፍልሰት ተመልሰዋል ተባለ፡፡

የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስተር ከሳውዲ፣ ከኦማን፣ከየመን እና ከሱዳን ከ90 ሺ በላይ ዜጎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን አስታውቋል፡፡

በሚኒስተር መስሪያ ቤቱ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከል እና የተመላሽ ዜጎች ድጋፍ እና ክትትል መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጄ ተክይበሉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ከሱዳን 47 ሺህ7 መቶ 46 ፣ ከሳውዲ አረቢያ 43 ሺህ 54 ፣ ከየመን ደግሞ 2 ሺህ 4 መቶ 82 እንዲሁም ከኦማን 2 ሺህ 1 መቶ 26 ዜጎች ተመልሰዋል።

የሚገቡ ፍልሰተኞችን ወደ አካባቢያቸው እንዲሸኙ እንደሚደረግ እና አካባቢቸው ባሉ ክልሎች በኩል ድጋፍ እንዲያገኙ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ከኦማን ከገቡ 2 ሺህ 1 መቶ 26 ፍልሰተኞች ውስጥም ሁሉም ወንዶች መሆናቸውን እና ከየመን ከተመለሱት ውስጥ ደግሞ 2 ሺ 59 ወንዶች ሲሆኑ 2 መቶ 71 የሚሆኑት ብቻ ሴቶች መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

የወንድ ከፍልሰት ተመላሽ ቁጥር የሚበዛበት ዋናው ምክንያትም መደበኛ ባልሆነ መንገድ የሚሄዱት አብዛኞቹ ወንዶች በመሆናቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከሄዱም በኋላ ወንዶች በብዛት ውጪ ላይ የጉልበት ስራዎች ስለሚሰሩ በፖሊሶች የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ ስለሆነ እና ሴቶች በብዛት የቤት ውስጥ ስራ ስለሚሰሩ እና ስለማይወጡ የመያዝ እድላቸው ዝቅተኛ በመሆኑ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

አሁን ባለው ሁኔታም ወጣቶች በተለያ ሁኔታ ከሀገር እየወጡ እንደሚገኙ እና ከሚደርሱት ይልቅ መንገድ ላይ የሚቀሩት ቁጥራቸው ከፍ እያለ መምጣቱን አስታውቀዋል፡፡

ወጣቶች ይህን በመገንዘብ መደበኛ የሆነውን የፍልሰት ስርአት ተከትለው እንዲወጡ የሚል መልእክታቸውንም አቶ ደረጄ አስተላልፈዋል፡፡

በሐመረ ፍሬው

ግንቦት 30 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply