ኩላሊት ከሞተ ሰው እንዲወሰድ የሚረዳ የህግ ማዕቀፍ እንዲኖር ቢጠየቅም እስካሁን መልስ አለመሰጠቱ ተነገረ፡፡የኩላሊት ንቅለ ተከላ ለማድረግ የኩላሊት ልገሳን ከቤተሰብ ውጭ እንዲለገስ የማ…

ኩላሊት ከሞተ ሰው እንዲወሰድ የሚረዳ የህግ ማዕቀፍ እንዲኖር ቢጠየቅም እስካሁን መልስ አለመሰጠቱ ተነገረ፡፡

የኩላሊት ንቅለ ተከላ ለማድረግ የኩላሊት ልገሳን ከቤተሰብ ውጭ እንዲለገስ የማይፈቅደው የኢትዮጵያ የጤና ህግ እንዲሻሻል ቢጠየቅም መልስ አለማግኘቱ ችግር ሆኗል ተብሏል።

የኩላሊት ተካሚዎች ማህበር በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሰፋ ኢትዮጵያ ውስጥ ኩላሊት ከሞተ ሰው እንዲወሰድ የሚረዳ የህግ ማዕቀፍ እንዲኖር ላለፉት ስድስት ዓመታት ቢጠየቅም እስካሁን ተግባራዊ መሆን አልቻለም ብለዋል።

ከቤተሰብ የሚደረገው የልገሳ ሂደትም በለጋሽ በኩል በሚያጋጥሙ ህመሞች እና ከለጋሽ ጋር ባለመመሳሰል ምክንያት የንቅለ ተከላ አለመሳካቶች ይስተዋላሉ ሲሉ አቶ አሰፋ ለጣቢያችን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ የአይን ብሌን ልገሳ ሰዎች በህይወት እያሉ ወደውና ፈቅደው በሚፈርሙት መሰረት ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ ልገሳ ማካሄድ እየተሰራበት እንደሚገኝ አንስተው ለኩላሊትም ተመሳሳዩን መደረግ ይገባዋል ብለዋል።

በሀገራችን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከኩላሊትና ከኩላሊት ጋር ከተያያዙ ህመሞች ጋር እንደሚኖሩ መረጃዎች ያመላክታሉ።

በለአለም አሰፋ

ሰኔ 04 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply