
ኩራባቸው ገብሬ (ኩራ) የተባለ የባልደራስ አባል መታሰሩ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 5 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አባል እና ንቁ ተሳታፊ የሆነው ኩራባቸው ገብሬ ጥር 4/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 አካባቢ በፖሊሶች መታሰሩ ተገልጧል። እስካሁን ፍርድ ቤት አለመቅረቡን ያስታወቀው ባልደራስ የግፍ እስረኛው አሁን ላይ በኮልፌ ክ/ከተማ ካራ ቆሬ ወረዳ 3 ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ ይገኛል ብሏል።
Source: Link to the Post