
በዚህ ሳምንት ማብቂያ ላይ ቅዳሜ ዕለት የእግር ኳስ አፍቃሪዎች በጉጉት የሚጠብቁት የዓለም ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ይካሄዳል። በዚህም ጨዋታ ምርጦቹ የፈረንሳይ እና የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድኖች ይፋለማሉ። የሁለቱ ቡድን ጨዋታ ታላቅ ከሚያደርጉት መካከል አንዱ የፈረንሳዩ ድንቅ ተጫዋች ኪሊያን ምባፔ ነው። በእግር ኳስ አፍቃሪዎችም ዘንድ ምባፔ አይረሴ ኮከብ ነው።
Source: Link to the Post