ኪ ሀውሲንግ ፋይናንስ ሶሊዩሽን በተጀመረ ዘጠኝ ወር ውስጥ ለ58 ባለዕድለኞች የቤት ባለቤት አድሪጊየለሁ አለ።ኪ -ሀውሲንግ ፋይናንስ ሶሊዩሽን ለኪ- ሲ ኤች ኤፍ ከ58 በላይ ለሆኑ ተመዝጋቢ…

ኪ ሀውሲንግ ፋይናንስ ሶሊዩሽን በተጀመረ ዘጠኝ ወር ውስጥ ለ58 ባለዕድለኞች የቤት ባለቤት አድሪጊየለሁ አለ።

ኪ -ሀውሲንግ ፋይናንስ ሶሊዩሽን ለኪ- ሲ ኤች ኤፍ ከ58 በላይ ለሆኑ ተመዝጋቢዎች የቤት ባለቤት ማድረግ መቻሉን በዛሬው ዕለት ገልጧል።

የኪ -ሀውሲንግ ፋይናንስ ሶሊዩሽን መስራችና ስራ አሰኪያጅ አቶ ግሩም ይልማ ድርጂታቸው በአነሰተኛ ወርሀዊ ቁጠባ በመቆጠብ ከወለድ ነፃ በሆነ የረጂም ጊዜ ክፍያ የመጀመሪያ ዙር ዕድለኛ አባሎችን የቤት ባለቤት አድርጊያለሁ ብለዋል።

አቶ ግሩም አሁንም አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ማንኛውንም ግለሰብ በአነስተኛ ወራዊ ቁጠባ እንዲከፍሉ በማድረግ ያለምን ቅድመ ሁኔታ በእጣ የቤት ባለቤት የሚሆኑበት ሁለተኛ ዙር ምዝገባ መጀመሩንም ተናግረዋል።

በተጨማሪም አቶ ግሩም ኪ -ሀውሲንግ ፋይናንስ ሶሊዩሽን ለኪ- ሲ ኤች ኤፍ ተመዝጋቢዎች ይበልጥ ተደራሽ ለመሆን እስካሁን በአጋርነት ከሚሰራቸው የባንክ አጋሮች በተጨማሪ ከቡና ባንክና ፀሐይ ባንክ ጋር አብሮ ለመሰማራት መስማማቱን አስታውቋል ።

የባንኮች ሚና ተመዝጋቢዎች በኪ ፋይናንስ ሶሊሽን ውስጥ አባል ሲሆኑ ቁጠባቸውን በዝግ አካውንት እንዲቀመጥ በማድረግ ሂደቱን ጠብቆ ለቤት ግዢ እንዲውል ማድረግና መከታተል ነው ተብሏል ።

በተጨማሪም ከባንኮቹ ሌላ በልዩነት ከአዲስ አበባ ሆቴልና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማህበር ጋር በአብጃታ ሻላ ትሬዲንግ ሀ/የተ/የግል ማህበር አመቻችነት አብረው ለመስራትና የማህበሩን አባላት የቤት ባለቤት የሚያደርግ የቅድመ ክፍያ አከፋፈል ስራዓት መዘርጋቱን አስታውቋል ።

በአብጃታ ሻላ ትሬዲንግ ሀ/የተ/የግል ማህበር የኪ -ሀውሲንግ ፋይናንስ ሶሊዩሽን ዋና ዋና አጋሮች መካከል አንዱ ሲሆን ቤቶችን በጥራትና በደረጃ እየገነባ ለባለዕድለኞች የሚያስተላለፍና የማርኬቲንግ አጋር በመሆን አባላቶች እየመዘገበ ያለ ማህበር ነው።

ኪ ሀውሲንግ ፍይናስ ሶልሽን በአሁን ጊዜ 17 ሺህ አባላት ሲኖሩት በሚቀጥሉት ሶስት ወራቶች አባላቶቹን ወደ 100 ሺህ አባላት ለማድረስ እቅድ እንዳለው ተናግረዋል።

በልዑል ወልዴ

ግንቦት 02 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply