ካህኑ በድንጋይ ተወግረው ተገደሉ!በአዲስ አበባ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ መጋቢት 14/2015 ዓ.ም ቀሲስ ዐባይ መለሰ የተባሉ ካህን ቅዳሴ ጨርሰው ወደ ቤታቸው በመሄድላይ እንዳሉ በድንጋይ ተወ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/Uim5XPyZLv0Qa7z_X4QAhjuOmm05st0Lm6OUpSfgDlT94_zuUD98vHByCSLPjX8XDW6GFW4mFNLkh4IdNP7vIGWuDIPx71fYcwSRGDihhFPlB2zxwOH_s2p2CPXLDc8bGVhwVAfXTIblg2rmCPKnDMnbDIlxiBzCM7yXmpnsz7GdxHIwdwhuJTbqjuFAKyDtvIVKUyabzo8JxGeCI93tcWP-bEOCECDW0CdwwP6KM9nEnBj6lpeejX3p3P0vVHAD429rTAAXy7wc3AKjiAxSKA9IysiH8fxvpCyGlJmT2MRnLfDE69oNtY6yUCCbd8VQ8uiWnnGHEslC_KaUQjrrog.jpg

ካህኑ በድንጋይ ተወግረው ተገደሉ!

በአዲስ አበባ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ መጋቢት 14/2015 ዓ.ም ቀሲስ ዐባይ መለሰ የተባሉ ካህን ቅዳሴ ጨርሰው ወደ ቤታቸው በመሄድላይ እንዳሉ በድንጋይ ተወግረው ሕይወታቸው ማለፉን የዐይን እማኞች እንዳረጋገጡለት የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ዘግቧል።

የሆርሲሳ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የነበሩት ቀሲስ ዐባይ መለሰ ሕይወታቸው ሲያልፍ ችግሩ ታወቀ እንጂ አስቀድሞ በአካባቢው አገልጋዮች ላይ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ይደርስ እንደነበር መረጃ ሰጭዎቻችን በቦታው ለተገኘው ዘጋቢያችን ገልፀዋል ብሏል ቴሌቪዥን ጣቢያው።

ካህኑ በድንጋይ ተደብድበው እያሉ ምስልና ቪዲዮ ለማስረጃ ለመያዝ ቢሞክሩም በአካባቢው የፀጥታ ኃይሎች ሞባይል እየተሰበሰበ መሰረዙንም ነግረውናል ብሏል።

@የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መጋቢት 15 ቀን 2015 ዓ.ም

ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን

Source: Link to the Post

Leave a Reply