
ካህኑ በድንጋይ ተወግረው ተገደሉ! መጋቢት 15 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ #Ethiopia | በአዲስ አበባ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ መጋቢት 14/2015 ዓ.ም ቀሲስ ዐባይ መለሰ የተባሉ ካህን ቅዳሴ ጨርሰው ወደ ቤታቸው በመሄድ ላይ እንዳሉ በድንጋይ ተወግረው ሕይወታቸው ማለፉን የዐይን እማኞች ገለፁ። የሆርሲሳ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የነበሩት ቀሲስ ዐባይ መለሰ ሕይወታቸው ሲያልፍ ችግሩ ታወቀ እንጂ አስቀድሞ በአካባቢው አገልጋዮች ላይ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ይደርስ እንደነበር መረጃ ሰጭዎቻችን ገልፀዋል። ካህኑ በድንጋይ ተደብድበው እያሉ ምስልና ቪዲዮ ለማስረጃ ለመያዝ ቢሞክሩም በአካባቢው የፀጥታ ኃይሎች ሞባይል እየተሰበሰበ መሰረዙንም ነግረውናል። ©ማኅበረ ቅዱሳን “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post