ካሜሮን በዓለም ደረጃ የመጀመሪያ ነዉ የተባለለትን የወባ ክትባት ዘመቻ ጀመረች፡፡በዓለም የመጀመሪያዉ ነዉ የተባለዉ የወባ ክትባት ዘመቻ በካሜሮን ተጀምሯል፡፡ይህ ፕሮግራም በአፍሪካ የሚገኙ በ…

ካሜሮን በዓለም ደረጃ የመጀመሪያ ነዉ የተባለለትን የወባ ክትባት ዘመቻ ጀመረች፡፡

በዓለም የመጀመሪያዉ ነዉ የተባለዉ የወባ ክትባት ዘመቻ በካሜሮን ተጀምሯል፡፡

ይህ ፕሮግራም በአፍሪካ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ህጻናትን ህይወት ለመታደግ ያሰበ መሆኑም ተገልጿል፡፡

አገሪቱ ለሁሉም ጨቅላ ህጻናት እና ዕድሜያቸዉ 6 ወራት ለሞላቸዉ ልጆች ሁሉ በነጻ ክትባቱን እየሰጠች መሆኑ ተዘግቧል፡፡

ክትባቱ 36 በመቶ የመስራት አቅም እንዳለዉ የተገለጸ ሲሆን ይህም ማለት ከሶስት ሰዎች የ 1ሰዉን ህይወት ማዳን ይችላል ፡፡

እንደ የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ በየዓመቱ በአፍሪካ 6መቶሺህ ሰዎች በወባ ምክንያት ህይወታቸዉ ያልፋል፡፡

ከሟቾች መካከል ደግሞ ዕድሜያቸዉ ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት 80 በመቶዉን ድርሻ ይይዛሉ፡፡

ባሳለፍነዉ ሳምንት የዓለም ጤና ድርጅት የቀድሞዋን ኬፕ ቨርዴ የአሁኑኗን ካቦ ቬርዲ የወባ በሽታን በማጥፋት ሦስተኛዋ የአፍሪካ አገር ሆናለች ሲል ዕዉቅና መስጠቱ የሚታወስ ነዉ፡፡

ሞሪሽየስ፣ አልጄሪያ እና ካቦ ቬርዲ ሶስቱ ከወባ ነጻ የሆኑ የአፍሪካ አገራት ናቸዉ፡

እስከዳር ግርማ

ጥር 13 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook  https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8

Source: Link to the Post

Leave a Reply