You are currently viewing #ካራማራ ኢትዮጵያዊውን የድል ቀን (ዳግማዊ ዓድዋ)! የካቲት 25 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የካቲት 23 ቀን 1970 ዓ.ም የዓድዋ ድል እለት የኢትዮጵያ ጦር በጭናቅሰን እና በቆሬ…

#ካራማራ ኢትዮጵያዊውን የድል ቀን (ዳግማዊ ዓድዋ)! የካቲት 25 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የካቲት 23 ቀን 1970 ዓ.ም የዓድዋ ድል እለት የኢትዮጵያ ጦር በጭናቅሰን እና በቆሬ…

#ካራማራ ኢትዮጵያዊውን የድል ቀን (ዳግማዊ ዓድዋ)! የካቲት 25 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የካቲት 23 ቀን 1970 ዓ.ም የዓድዋ ድል እለት የኢትዮጵያ ጦር በጭናቅሰን እና በቆሬ በኩል ወደ ጅጅጋ አቅጣጫ የተጠናከረ ቅንጅታዊ የጎህ መጥቃት ዘመቻ ከፈተ። የሶማሊያ ጦርም ጥቃት ይመጣብኛል ብሎ ብሎ ካልጠበቀው አቅጣጫ በመወጋቱ ተደናገጠ። ጅጅጋንም ላለመልቀቅ ተሟሟተ። ሶማሊያ በዚህ መደናገጥ ውስጥ እያለች ከጀልዴሳ ግንባር ሌላ ጥቃት ተከፈተባት። የሶማሊያም ሰራዊት ጅጅጋን ከለቀቀ ትልቅ የሞራል ውድቀት እንደሚገጥመው ያውቃል። በመሆኑም ከጅጅጋ በስተምእራብ በኩል ባለው ካራማራ ተራራ ላይ ማዘዣ ጣቢያውን በመስራት በከፍተኛ ደረጃ ተከላከለ። ሆኖም በለስ አልቀናውም። ጥቃቱ በሁሉም ግንባር የተከፈተ በመሆኑ አጋዥ ሰራዊት ከየትም ማንቀሳቀስ አልቻለም። በውጤቱም የካቲት 26 ረፋድ ላይ በካራማራ ከባድ ሽንፈት ተጎነጨ። በውጤቱም ከሞትና መቁሰል የተረፈው የጠላት ሠራዊት መሳሪያውን እያንጠባጠበ ጅጅጋን በመልቀቅ ወደ ሀርጌሳ መስመር ፈረጠጠ ። እሁድ የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም ላይ በአከባቢው የነበረ ሰራዊት ወድቃና ተዋርዳ የነበረችውን የሀገራችን ሰንደቅ አላማ መልሶ ከፍ አድርጎ በክብር ሰቀለ። የዛሬ 45 አመት እንዳይድን እንዳይሽር ተደርጎ የተሰበረው የዚያድባሬ ተስፋፊ ኃይል በቀጣይ ቀናቶች ጦርነቱን በይፋ አቁሞ በወረራ ተቆጣጥሯቸው ከነበረው ከቀሪ የኢትዮጵያ ሉኣላዊ መሬቶች ተጠቃሎ ወጣ። ይህ ድል እውን እንዲሆን ግን የበርካታ ውድ ኢትዮጵያዊያን የደምና የአጥንት መስዋእትነት አስፈልጎ ነበር። ከኢትዮጵያዊያን በተጨማሪም የወንድም ህዝብ ልጆች የሆኑት የኩባዊያንና የደቡብ የመናዊያን ውድ የህይወት መስዋእትነት ተከፍሎበታል። ➻ የደረሰው ጉዳት በአጭሩ ይህን ይመስላል።ሠራዊት የሞተ የቆሠለ የተማረከ ኢትዮጵያ18,000፨29,000 ፨ 450 ኩባ 163 1 የመን 100 ሶማሊያ15,900፨26,200፨ 1,785 የካራማራ ድል ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ሉአላዊነት ያላቸውን ቀናኢነት ቀፎ እንደተነካ ንብ በህብረት በመቆም ገልፀውታል ። ለሠንደቃቸው ያላቸውን ልባዊ ፍቅር ውድ መስዋዕትነት በመክፈል በደማቅ የደም ቀለም ፅፈውታል። ለዘመናት የተገመደው የማይበጠስ አንድነታቸውን በደም ፍሳሻቸውና በአጥንት ፍላጫቸው በድጋሚ በፅኑ መሠረት ላይ ገንብተውበታል። ከታላቁ የዓድዋ ድል ቀጥሎ የኢትዮጵያዊያን ህብረትና አንድነት ማሳያ የሆነው የካራማራ ጦርነት ለማመን የሚቸግሩ በጀብድ የተሞሉ ጀግንነቶች በተናጠልና በቡድን ተከናውነውበታል። ተዘርዝረው ከማያልቁ የሠራዊቱ ጀብዶች መካከል ለምሳሌ ያህል ሁለቱን ልጥቀስ። የሀረር አካዳሚና የበረራ ት/ቤት ጥምር ምሩቅ የሆኑት የአዲስ አበባው ፍሬ የአየር ኃይሉ ነብር ጀግናው ብ/ጀ ለገሰ ተፈራ በF5-E ጀታቸው አማካይነት በአየር ላየር ላይ ውጊያ አምስት የሶማሊያ ሚግ 21 ጀቶችን በመምታት ከአየር ወደ መሬት አራግፏቸዋል። በርካታ ጀብድ ፈጽመው የድሉ መጨረሻ ሰአት ላይ በፊልቱ ግንባር ላይ አውሮፕላናቸው ተመትቶ በጠላት ተይዘው ለ11 አመታት በሶማሊያ እስር ቤቶች የስቃይ ህይወት አሳልፈው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። ለወደር የለሽ የጀግንነት ስራቸውም በጊዜው የሀገሪቱ የመጨረሻ ደረጃ የሆነውን የህብረተሠባዊት ኢትዮጵያ ወደር የለሽ የጀግና ሜዳይ ተሸልመዋል ። እንኳን ለካራማራ ኢትዮጵያዊውን የድል ዋዜማ ቀን አደረሳችሁ! “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply