ኬሪያ ኢብራሂም፣ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ እና ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማን ጨምሮ የህወሓት ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ከእስር ተፈቱ

በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል እና በሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ መዝገብ ተከስሰው በእስር ላይ የነበሩ የህወሓት ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 21፤ 2015 አመሻሽ ላይ ከእስር መፈታታቸውን የተከሳሾቹ ጠበቆች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሃፍቶም ከሰተ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። በዛሬው ዕለት ከእስር ተለቅቀው ወደ ቤታቸው መግባታቸው ከተረጋገጡ ተከሳሾች ውስጥ፤ የህወሓት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ እና ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማ እንደሚገኙበት ጠበቃው አስታውቀዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

The post ኬሪያ ኢብራሂም፣ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ እና ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማን ጨምሮ የህወሓት ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ከእስር ተፈቱ appeared first on Ethiopia Insider.

Source: Link to the Post

Leave a Reply