ኬንያ ለኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች አገልግሎት የሚውለውን የኮልታን ማዕድን ክምችትን ማግኘቷን አስታወቀች፡፡ምስራቅ አፍሪካዊቷ ሃገር ውድ ዋጋ አለው የሚባለውን ኮልታን የተሰኘውን ማዕድን…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/DsqTE9qdPw1bQsqqkuCAt10TFQG2u1Thfz1zI5y8Tp83nMKUiqIqKxcR4K05FOrMPwtlhp-UMALU-K8YalZBuiv-MBoKAxjXIvZuUPyMsj0AGdglEaGJFTTccXiy6aLLpH5ftM1TDw8NNvQ9Nhh2djiBlsjJIcB16GvrWFlHo3qOEGafBObOxlvV52PTH9TwliTpZ3xvKcywZL-1kmpgS6BRJ2cayrATySXjHrRozOTQJtVjqujDXRlz32o_6DONlS1Y4lDJaCHxhA4ik1Y7WZgN0H1YThQTXd4L6psms0PSyzOjFxQrqxooghKl4V109lyC6ek6Vqb2RqQlLxWLsA.jpg

ኬንያ ለኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች አገልግሎት የሚውለውን የኮልታን ማዕድን ክምችትን ማግኘቷን አስታወቀች፡፡

ምስራቅ አፍሪካዊቷ ሃገር ውድ ዋጋ አለው የሚባለውን ኮልታን የተሰኘውን ማዕድን ማግኘቷን አስታወቀች።

የኬንያ ማዕድን ሚኒስቴር ሃገሪቱ የኮልታን ማዕድን ክምችት ማግኘቷን አስታውቋል።

ማዕድኑ ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ባትሪ፣ የሞባይል ስልክ ቀፎ እና ሌሎች ውድ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን ለማምረት እንደሚያገለግል ቢቢሲ አስነብቧል።

በሃገሪቱ ስድስት አካባቢዎች የተገኘው የማዕድኑ ክምችት መጠን ምን ያክል እንደሆነ ግን የተባለ ነገር የለም።

ሌላኛዋ አፍሪካዊት ሃገር ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዓለም ላይ ካለው የኮልታን ክምችት ከ70 በመቶ ያህሉ እንዳላት ሲገመት ሩዋንዳ ሁለተኛዋ ከፍተኛ የማዕድን ክምችት ካላቸው የአፍሪካ ሀገራት አንዷ መሆኗን መረጃዎች ያመላክታሉ።

የዚህ ማዕድን መገኘት ለሀገሪቱ ተጨማሪ የሥራ እድሎችን ለመፍጠር እንደሚያስችል ታምኖበታል።

የ 1 ኪሎ ግራም የኮልታን ማዕድን ዋጋ እስከ 48 የአሜሪካ ዶላር ዋጋ እንደሚደርስ ይታመናል።

በልኡል ወልዴ

ጥር 16 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply