በአዲስ አበባ የሚገኙ 75 የመንግስትና ከግል የመጡ ከ500 በላይ ተማሪዎችን በ አስራ አንድ ጉዳዮች ላይ በማተኮር አንድ ነጥብ አምስት ሚልየን ብር በመበጀት የነፃ ስልጠና ሰጥቷል ።
የክቡር ኮሌጅ ፕሬዝዳንት
አቶ ደሳለኝ መኩሪያ ባለፈው ቅዳሜ በአዶት ሲኒማ በነበረው ማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ እንዳሉት ተማሪዎች በኮሮና ምክንያት ወደ ዩንቨርሰቲ የሚገቡ ተማሪዎች ማ በህይወት ክህሎት ዙርያ ማግኘት ያለባቸውን ነገር አላገኙም ብለዋል።

ተማሪዎቹ በአመራርነት ፣በስራ ፈጠራነት፣ በሰሜት ብልህነት፣ በንግግር ክህሎት ፣በዌብ ዴቨሊፕመንት ፣ግራፊክስ ፣ ሮቦቶኪስ በመሳሰሉት ዘርፎች ስልጠናም እንደወሰዱ አቶ ደሳለኝ ተናግረዋል።
” እንደ ዜጋ ተማሪዎች መቀየር ሀገር መለወጥ ነው ብለን እናምናለን። ቤተሰብ አካዳሚ የሚባል ት/ ቤት አለን ። የእኛን ተማሪዎች ብቻ ማሰልጠን በቂ አይደለም ። ምክንያቱም ተማሪዎቻችን ዩንቨርስቲ ሲገቡ ብቻቸውን አይደለም ።ለዛም ነው 74 ት/ ቤት ተማሪዎችን ጨምረን ያሰለጠነው። ” ብለዋል።
The post ክቡር ኮሌጅ ለዩንቨርስቲ ገቢ ተማሪዎችን የህይወት ክህሎት ስልጠና በነፃ ሰጥቷል። appeared first on Fidel Post.
Source: Link to the Post