
ክብር ለእርስዎ ይሁን.. <<ቤተክርስትያን በአሏህ የተመሰለች ናት፤ አሏህ አንድ ነው፣ አሏህ አይከፈልም ኦርቶዶክስ ኃይማኖትም ጥንትም አንድ ናት ዛሬም አንድ ናት አትከፈልም! ~~~~ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እንድሪስ ~~~~ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ከጥንት ጀምሮ በታሪክ የምንሰማው እኛም በእድሜያችን የተመለከትነው ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ሰላማዊ እንግዶችን በክብር ስትቀበል፣ ከሌላው ኃይማኖት ጋር ተከባብራ አብራ ስትኖር፣ ህመም ወረርሽኝ ሲመጣ፣ በሃገር ላይ ጦርነትና ሃዘን ሲመጣ ዱኣ አድርጋ ስትታደግ፣ አንድ ሆና ሃገርን አንድ ስታደርግ ነው። የቤተክርስትያኗ አባቶችም አንድም ቀን እንኳን ሊለያዩ ቀርቶ አንድ አካል አንድ አምሳል ሆነው አባት ልጁን ልጅም አባቱን አክብረው ከመኖር ያለፈ በመሃላቸው ልዩነት ተፈጥሮባቸው አይተን አናውቅም። ዛሬ ልጆች ከአባቶቻቸው ለመለየት የሚያበቃ ምን ተገኘና ነው አባቶቻቸውን አስቀይመው አሳዝነውና አስለቅሰው ለመለየት የፈለጉት? አባቱን የናቀ ሁሉ አላህን የናቀ ነው፣ አባቱን ያከበረ ሁሉ አላህን ያከበረ ነው። አባቶችን ንቆ እነርሱ ያቆሟትን ጥንታዊና አንድ የነበረችዋን የኦርቶዶክስን ሃይማኖት በመክፈል ከአባቶች መለዬት ማለት ከአላህ መለዬት ማለት ነው። ኧረ ተው! ይሄኮ አላህን ለማስቆጣት መቻኮል ነው! እኔ እስከገባኝ ድረስ ቤተክርስትያን በአሏህ የተመሰለች ናት፣ አሏህ አንድ ነው፣ አሏህ አይከፈልም፣ አሏህ አንድ ሁኑ ተደጋገፉ በአንድነት ድመቁ ይላል። ኦርቶዶክስ ኃይማኖትም ጥንትም አንድ ናት ፤ ዛሬም አንድ ናት አትከፈልም።>> ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ኡመር እድሪስ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post