#ክትባቱ ከዛሬ ጀምሮ በዘመቻ ይሰጣል!የማህፀን በር ካንሰር በሽታ መከላከያ ክትባት ከዛሬ ጀምሮ በዘመቻ እንደሚሰጥ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ክትባቱ ከዛሬ ጀምሮ “ክትባት የሁሉንም ማህበረ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/C3lnQf5KuS_5t2xiMJq_fWvEFRgVuzk6xEj2CI-lL5d4v1jSH2r13LX2XptqnuN4ikj1Bw9AVDiDFTNModzXRDoi654fu2bS7WQyGo-Cs1URyj9o-45Vv55-LO0XAhQX24Cq2Y1Wsifya-CAwJaOSQfGLi73z6I03_eylLx-HlhgTjOEegVPzNA4VlF3VYRxKC2E4Cg5pYDsn31V1xV0if2Mb7wx82e1J9IU5xOTynr9-fi4aEa_7PwinI0XjJF_US9R79VIjyZBWpX4pjA20142bhARobNLFKSI2Ure3acJ0N8iLGEV9cPkcACcxgxAS3HkQ1MspHdRUTVNv1uW0g.jpg

#ክትባቱ ከዛሬ ጀምሮ በዘመቻ ይሰጣል!

የማህፀን በር ካንሰር በሽታ መከላከያ ክትባት ከዛሬ ጀምሮ በዘመቻ እንደሚሰጥ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ክትባቱ ከዛሬ ጀምሮ “ክትባት የሁሉንም ማህበረሰብ ጤና ለማስጠበቅ” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ በዘመቻ እንደሚሰጥ የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በኢትዮጵያ በዓመት በማህጸን በር ካንሰር ምክንያት ከ5ሺሕ በላይ ሴቶች ህይወታቸው የሚያልፍ መሆኑን ገልፅዋል።
ዕድሚያቸው ከ14 ዓመት በላይ ከሆኑት ሴቶች ከአምስቱ አራቱ በህይወት ዘመናቸው ለማህፀን በር ካንሰር ተጋላጭ እንደሚሆኑም ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡

የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በዓመት 2 ጊዜ በ6 ወር ልዩነት ሁለት ዶዝ ክትባት ሲሰጥ መቆየቱንም ጠቅሰዋል፡፡

በ2016 ዓ.ም ከ1.5 ሚሊዮን የሚጠጉ እድሚያችው 14 አመት የሆናችው ሴቶች ልጆች ለመከተብ የታቀደ ሲሆን ክትባቱ በትምህርት ቤቶች፣ በጤና ተቋማት እና በጊዜያዊ ክትባት መስጫ ጣቢያዎች የሚሰጥ መሆኑ ታውቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 25 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply