ኮሚሽነር አበረ አዳሙ እዉነተኛ የህዝብ ልጅ ነበር ፦ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ባህርዳር ። ሚያዚያ 28/2014/ አሻራ ሚዲያ በትናትዉ ዕለት በኮሚሽነ…

ኮሚሽነር አበረ አዳሙ እዉነተኛ የህዝብ ልጅ ነበር ፦ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ባህርዳር ። ሚያዚያ 28/2014/ አሻራ ሚዲያ በትናትዉ ዕለት በኮሚሽነር አበረ አዳሙ ማስታወሻ የመፅሐፍ ምርቃት የተገኙት አቶ ገዱ አንዳርጋቸዉ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ እዉነተኛ የህዝብ ልጅ ነበር ያሉ ሲሆን ግልፅ መሆን ብቻ ሳይሆን የሚሰማዉን በድፍረት በጀግንነት የሚያቀርብ ታጋይነትን እንደ ክብር የሚመለከት ሰዉ ሰለነበር ለወደፊቱ ትዉልድ ምን አልባትም አሁን ሀገራችን የገጠማትን ችግር ህዝባችን የገጠመዉን ችግር ከስር መሰረቱ ለመፍታት እንዲህ አይነት የወሰኑ ሰዎች ያስፈልጋሉ በንግግር ሳይሆን እንዲሁ ለመታየት ሳይሆን ከልብ በመነጨ ሁኔታ እራሳቸውን በጊዜም በጉልበትም በዕውቀትም እንደገናም የባሰዉ ከመጣ መስዋዕት ለማድረግም የቀረጡ ሰዎች ያስፈልጋል ኮምሽነር አበረ አዳሙ ያደረገዉ ይህን ነዉ ብለዋል ። ኮሚሽነር አበረ አዳሙ በአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ብቻ ያደረገው ትግል ብቻ ሳይሆን ቀድሞውን በኤርትራ በረሀ የገባበት የተሸላ ሰላም በኢትዮጵያ እንዲፈጠር በተለይም የዲሞክራሲ ስርዓት እንዲፈጠር ሰዉ ሀሉ እኩል ሁኖ በህግ የበላይነት የሚተዳደርበት ሁኔታ ለመፍጠር በቃል ሳይሆን በተግባር ለማዋል ከፋተኛ ጥረት አድርገዋል ሲሉም አክለዋል ። የኮሚሽነር አበረ አዳሙን በህይወት ዘመኑ የሰራዉን ስራ ለትዉልድ ለማስተላለፍ ያለምንም ነገር በራስ ተነሳሽነት በራስ ወጪ ሌት እና ቀን በድፍረት ይህን መፅሐፍ ለፃፈዉ ለዶክተር ሞላ ፈለቀ ምስጋና ይገባቸዋል ያሉት ደግሞ የገቢዎች ሚኒስቴር አቶ ላቀ አያሌዉ ናቸዉ። አቶ ላቀ አያሌው አክለዉም በህይወት እያለም በህይወት ሳይኖርም እዉቅና የሚሰጥ መሪ ካለ ነገ በርካታ መሪዎች ህይወታቸውን አሳልፈዉ የሚሰጡ ጀግኖች ሊፈጠሩ ይችላሉ ብለዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply