ኮሚሽኑ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከክልሎች ጋር የቀጣይ ዓመታት የአረንጓዴ አሻራና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃን ለማጠናከር የሚረዳ ስምምነት ፈጸመ።

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2013 ኮሚሽኑ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከክልሎች ጋር የቀጣይ ዓመታት የአረንጓዴ አሻራና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃን ለማጠናከር የሚረዳ ስምምነት ፈጸመ። የአካባቢ፣ የደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ኮሚሽኑ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከክልሎች ጋር የቀጣይ ዓመታት የአረንጓዴ አሻራና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃን ለማጠናከር የሚረዳ ስምምነት ማድረጉን አስታዉቋል፡፡

በሂደቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና የክልሎችን ተሳትፎ በማሳደግ በአንድ በኩል የክልሎችን አቅም ለማጎልበት በሌላ በኩል የምርምር ተቋማቱ የልህቀት ማዕከላት ለመሆን የስራውን ቀጣይነት እንዲያረጋግጡ ማስቻል ነው። የአካባቢ፣ የደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕ/ር ፍቃዱ በየነ እንዳሉት የሀገር ልማትና ብልፅግናን ቀጣይነት የሚረጋገጠው የከፍተኛ ትምህርትና ምርምር ተቋማት የነቃ ተሳትፎ ሲኖር መሆኑን ገልፀው ኮሚሽኑ ይህንኑ እምነት በመያዝ ከናንተ ጋር በጋራ ለመስራት ወስኗል ብለዋል።

በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አምስት ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል የታቀደ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ለጎረቤት ሀገራት የሚደርስ የአንድ ቢሊዮን ችግኞችን አፍልቶ ለማከፋፈል እቅድ ተይዟል። በእቅዱም ኤርትራ፣ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ጅቡቲ፣ ኬንያና ሶማሊያ የሚካተቱ ሲሆን ለነዚህ
ሀገራት ከስነ ምዳራቸው እና ከአየር ንብረታቸው ጋር በተጣጣመ ሁኔታ የሚስማሙ ችግኞች እደሚዘጋጅላቸዉተገልጿል፡፡ ዋቻሞ፣ ሰመራ፣ ጅግጅጋ፣ ባህር ዳር፣ ሀረማያና ወለጋ ዩኒቨርሲቲዎችም በመጀመሪያው ዙር ስራውን ከክልሎች ጋር በመቀናጀት በምርምር እንዲደግፉ ተመርጠው ስምምነት ተደርሷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply