ኮማንድ ፖስትና ብሔራዊ ደኅንነት ጣልቃ ቢገቡም የወርቅ ኮንትሮባንድ ሊቆም አልቻለም ተባለ፡፡በመከላከያ ኮማንድ ፖስትና በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ጭምር ክትትል ቢደረግም፣ በክልሎች…

ኮማንድ ፖስትና ብሔራዊ ደኅንነት ጣልቃ ቢገቡም የወርቅ ኮንትሮባንድ ሊቆም አልቻለም ተባለ፡፡

በመከላከያ ኮማንድ ፖስትና በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ጭምር ክትትል ቢደረግም፣ በክልሎች እየጨመረ የመጣው የወርቅና የማዕድናት ኮንትሮባንድ ሊቆም እንዳልቻለ ተነግሯል፡፡

በማዕድናት ሕገወጥ ግብይት፣ ኮንትሮባንድና የፀጥታ ችግር ምክንያት በባለፉት ዘጠኝ ወራት ወደ ብሔራዊ ባንክ የገባው ወርቅ ሦስት ቶን ብቻ እንደሆነ፣ ይህም ከዕቅዱ 50 በመቶ ብቻ መሆኑ ታውቋል፡፡

የወርቅ ገቢም ከታቀደው 363 ሚሊዮን ዶላር 67 በመቶ ብቻ መሳካቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በመጋቢት ወር ብሔራዊ ባንክ የገባው ወርቅ 350 ኪሎ ግራም ሲሆን፣ ይህም በ2014 ዓ.ም. መጋቢት ወር ከተገኘው 800 ኪሎ ግራም በእጅጉ ያነሰ ነው ተብሏል፡፡

በአገሪቱ ያሉ ወርቅ አምራቾች የባህላዊና የኩባንያ ተብለው ሲከፈሉ፣ በተለይ በባህላዊ አምራቾች የሚወጣው ወርቅ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ወደ ብሔራዊ ባንክ መግባት ያቆመ መሆኑን፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከታቀደው 2‚306 ኪሎ ግራም ውስጥ 609 ኪሎ ብቻ (26 በመቶ) መቅረቡን መረዳት ተችሏል፡፡

እንደ ሪፖርተር ዘገባ በተለይ ኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች ለብሔራዊ ባንክ ለማቅረብ ካቀዱት አንፃር የቀረበው እጅግ አናሳ መሆኑን፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የማዕድን ሚኒስቴር ሪፖርት ያሳያል፡፡

ይሁን እንጂ ፈጽሞ ወርቅ ካላቀረቡት የትግራይ፣ የአፋር፣ የደቡብ ኢትዮጵያና የሶማሌ ክልል አንፃር የበፊቶቹ እንደሚሻል ሪፖርቱ ያሳያል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 22 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply