ኮሮናቫይረስ በአውሮፓ የገደለው ሰው ብዛት 500,000 አለፈ !

በአውሮፓ ከተከሰተ አመት ሊሞላው የወራት እድሜ የቀረው ኮሮናቫይረስ አስከአሁን በአህጉሩ ከ500,000 በላይ ሰው ሲገድል ከ 23 ሚልየን ሰው በላይ ደግሞ ቫይረሱ አንደተገኘበት የፈረንሳዩ ዜና ወኪል ኤኤፍፒ መረጃ ያሳያል።

በአህጉሩ በቫይረሱ ከሞቱት ውስጥ ግማሹ በስፔን ፣ጣሊያን ፣ብሪታንያ እና ፈረንሳይ ነዋሪ የነበሩ ሰዎች ናቸው።

የሞቱ መጠን በአህጉር ደረጃ በአለም ከፍተኛው ሲሆን ላቲን አሜሪካና ካረቢያን ደሴቶች 477,404 ሞት ሲያስመዘገቡ አሜሪካና ካናዳ 321,287 ሰው በቫይረሱ አጥተዋል።

በአንፃሩ በአፍሪካ ፣በኤዥያና በመካከለኛው ምስራቅ በቫይረሱ የሞተው ሰው በአንፃሩ ሲታይ አነስተኛ ነው።

The post ኮሮናቫይረስ በአውሮፓ የገደለው ሰው ብዛት 500,000 አለፈ ! appeared first on Fidel Post.

Source: Link to the Post

Leave a Reply