ኮስሞፖሊታን ሪል እስቴት ያስገነባቸው ቤቶች አስመረቀ።ድርጅቱ በቦሌ ሩዋንዳ ኤንባሲ አካባቢ ያስገነባውን ጂ +11 የሆነ በ 700 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈውን ዘመናዊ አፓርታማ በትናንትናው ዕለት…

ኮስሞፖሊታን ሪል እስቴት ያስገነባቸው ቤቶች አስመረቀ።

ድርጅቱ በቦሌ ሩዋንዳ ኤንባሲ አካባቢ ያስገነባውን ጂ +11 የሆነ በ 700 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈውን ዘመናዊ አፓርታማ በትናንትናው ዕለት አስመርቋል።

በምረቃ ስነስርአቱ ላይ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን  ለቤት ባለቤቶች ቁልፍ አስረክቧል።

የስፖርት ማዘውተሪያ ጂም፣ ሳውናና ስቲም የተሟላላቸው ሲሆን መኖሪያ ቤቶች የ24 ሰዓት ኤሌክትሪክም ተመቻችቶላቸዋል ተብሏል።

ድርጅቱ የመኖሪያ ቤት ችግር ለማቃለል የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ የሚገኝ ድርጅት መሆኑን በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ ተገልጧል።

ኮስሞፖሊታን የስሙ ትርጉም በአንድ ቦታ ተሰባስቦ የሚኖር የከተማ ማህበረሰብን የሚያመለክት መሆኑን የጅርጅቱ ባለቤት አቶ ዮናስ ካሳ ተናግረዋል።

የኮስሞፖሊተን መኖሪያ ቤቶች በሙያው የላቀ ልምድ ባካበቱ የአገር ውስጥና የውጭ ባለሙያዎች የተገነቡ ናቸው ተብሏል።

የግንባታ ስራው ሲያከናውን ከ250 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏልም ብለዋል።

በተጨማሪም ኮስሞፖሊታን፣ኦሎምፒያ ጂ+17 ሀንጻ እንዲሁም በፒያሳ ካቴድራል አካባቢ ለሱቅና ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የገበያ ማዕከል ግንባታ በቅርቡ የሚጀምር ሲሆን ለበርካታ ኢትዮጵያዊያን የስራ ዕድል እንደሚፈጥር ተነግሯል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

Source: Link to the Post

Leave a Reply