ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ እያሻቀበ ነው

ኢትዮጵያ ውስጥ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ባለፉት ሁለት ሣምንታት ከሦስት በመቶ ወደ ሃያ ስምንት ከመቶ ማሻቀቡን የጤና ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

በአንድ ሣምንት ጊዜ ውስጥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከስምንት ሺህ በላይ መውጣቱንና የሥርጭቱ መጠን በስፋት መጨመሩን የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልፀዋል።

በዓለም ላይ የተከሰተው ኦሚክሮን የኮሮናቫይረስ ዝርያ ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር አለመኖሩ በባለሙያዎች እየተፈተሸ መሆኑን ሚኒስትሯ አክለው ገልፀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ።

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply