ኮካኮላ ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ በመጀመሪያ ዙር ከ25ሺህ የንግድ ባለቤቶች መካከል ዕጣ ለወጣላቸዉ 70 ግለሰቦች የፍሪጅ ሽልማት አበርክቷል፡፡
ሽልማቱ በትናንትናው ዕለት በብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር አዳራሽ የወጣ ሲሆን የመጀመሪያዎቹ አስሩ ዕጣዎች በአካል ቀሪዎቹ 60 ደግሞ በኦንላይን የወጡ ናቸዉ፡፡
ከአንድ ወር በኋላ ሁለተኛዉን ዙር እንቀጥላለን ሲሉ የተናገሩት የኮካኮላ ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ማርኬቲንግ ማኔጀር ወይዘሪት አብነት ጸጋዬ፤ እስከ ህዳር 22 ድረስ የሚቀጥል መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
አክለዉም የዕጣ ማዉጣት ስርዓቱ በአዲስ አበባ እስከ 6 ወር ድረስ ለመቀጠል መታሰቡን አንስተዉ በቀጣይ ወደ ክልል ከተሞችም ለመሄድ መታቀዱንም ገልጸዋል፡፡
በብዛት ምርቶቻችንን ሱቆች እና ምግብ ቤቶች ናቸዉ የሚጠቀሙት ያሉት ማርኬቲንግ ማኔጀሯ፤እነዚህ ተቋማትም በብዙ የኑሮ ዉድነት ጫና ዉስጥ እያለፉ በመሆኑ ስራቸዉን የሚያቀላጥፍ ድጋፍ ነዉ ያደረግነዉ ብለዋል፡፡
ከዚህ በፊት ተጠቃሚዎችን ባለዕድል የሚያደርጉ ሽልማቶችን ስንሸልም ቆይተናል ያሉት ወይዘሪት አብነት፤ አሁን ደግሞ የንግድ ባለቤቶችን ለማበረታታት ይህን ሽልማት አስጀምረናል ነዉ ያሉት፡፡
ብዙዎች ተሳታፊ እንዲሆኑ በማሰብ መስፈርቱን የተጋነነ አላደረግነዉም ያሉት ማርኬቲንግ ማኔጀሯ 5ሳጥን ወይም 5 እሽግ አልያም 3የፋንታ ኦሬንጅ ሳጥን ወይም 3 እሽግ ሲገዙ የዕጣ ኩፖኖች እንደሚሰጡ ተናግረዋል፡፡
ኮካኮላ ነሃሴ 29 ያስጀመረዉን ለ2መቶ የንግድ ባለቤቶች ፍሪጆችን እና ለ25ሺህ ባለዕድለኞች ደግሞ የነጻ መጠጥ የመስጠት ፕሮግራም የመጀመሪያ ዙር እድለኞችን ነዉ በዛሬዉ ዕለት ይፋ ያደረገዉ፡፡
በእስከዳር ግርማ
ጥቅምት 15 ቀን 2016 ዓ.ም
ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video
Source: Link to the Post