ኮካኮላ ቤቬሬጅስ አፍሪካ -ኢትዮጵያ ከ 8መቶ በላይ አባወራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የመጠጥ ውሃ ቦኖዎች እና የኤሌክትሪክ ሃይል ማሰራጫ መስመር አስገንብቶ አስረክቧል።
ኮካኮላ ባለፈው አመት ባስመረቀው እና ሰበታ ዲማ በሚገኘው ፋብሪካው አከባቢ ለሚኖሩ ማህበረሰቦች ነው በዛሬው ዕለት እነዚህን መሠረተ ልማቶች ገንብቶ ያስረከበው።
የተገነባው የንፁህ ውሃ መጠጥ ቦኖ ህብረተሰቡ የንፁህ ውሃ ለማግኘት የሚያደርገውን የእግር ጉዞ በማሳጠር የዕለት ተዕለት ኑሯቸውን የሚያቀላጥፍ ይሆናል ነው የተባለው።
ኩባንያው አንድ ኪሎ ሜትር የውሃ መስመር በመዘርጋትና የማከፋፈያ ቦኖዎችን በመዘርጋት የአካባቢውን የመጠጥ ውሃ ችግር ለመቅረፍ ከፍተኛ አስተዋፆ ማድረጉን የገለፁት የወረዳው አስተዳዳሪ ናቸው።
በተመሳሳይ ሁኔታ ኩባንያው ከሰበታ ፋብሪካ የተሰጠ 1.2 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ትራንስፎርመር እንዲሁም 6መቶ ሺህ ብር የሚያወጡ የተለያዩ ቁሳቁሶችና የግንባታ ወጪን በመሸፈን ከ150 በላይ የሚሆኑ የአካባቢው አባወራዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረጉም ነው የተገለፀው።
ኩባንያው ከዚህ በተጨማሪ ለ 3 ወራት በሞግዚትነትና ቤት አያያዝ ያሰለጠናቸውን 50 ሥራ አጥ ሴቶችን አሰልጥኖ ማስመረቁንም ለማወቅ ተችሏል።
“ኮካ ኮላ በኢትዮጵያ ከስድስት አስርት ዓመታት በላይ በአብሮነት የቆየና ጠንካራ የሀገር ውስጥ ቢዝነስ መገንባት የቻለ ተቋም ነው ያሉት የሲሲቢኤ- ኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዳረል ዊልሰን ናቸው።
ይህም እያደገ በሄደ ቁጥር ለህብረተሰቡ እና ለሰራተኞች የጋራ እድል ፈጥሯል” ሲሉ ተናግረዋል።
ሲሲቢኤ ኢትዮጵያ በ236 ሺህ ዶላር በሰበታ ትምህርት ቤት ገንብቶ ማስረከቡም የሚታወስ ነው።
እስከዳር ግርማ
መስከረም 22 ቀን 2016 ዓ.ም
ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video
Source: Link to the Post