ኮኬይን የተባለ አደገኛ ዕፅ ውጠው የተገኙ የብራዚልና የኢንዶኔዥያ ዜግነት ያላቸው ተጠርጣሪዎች በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ሥር ዋሉ::ኮኬይን የተባለ አደገኛ ዕፅ ውጠው የ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/feKGfnsNCf8KEg0cn3E8be6HaADyPlAX9f6jSXlG77pBAQL4Lexn47MmvLzOKIemllkHG-rqJf9Gev35zWqU9GP8go_CdQDBCnLgQBDBLq1PXNOBnqgM_8pzb13Evo1w6JGiH_30TPXylTJWNJch-Oj00noC585vWqA0ONthZiE6YabD1zDMTMj3e9T0OmC9mVPa6Rgb0xCVqwEo-lfQOdUPcCR9qhAjQ-9tw8EzKvJcSp_YwZ0S_1Vlr_HTEaumVR5C9T2PL8trllsdJwuGAP3uaRrFkYjW1HFjL9_o3hw06p5sE5KcSkyCxABOnnrVq8u5CmFKeNFfFZ-Bjaqrxg.jpg

ኮኬይን የተባለ አደገኛ ዕፅ ውጠው የተገኙ የብራዚልና የኢንዶኔዥያ ዜግነት ያላቸው ተጠርጣሪዎች በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ሥር ዋሉ::

ኮኬይን የተባለ አደገኛ ዕፅ ውጠው የተገኙ የብራዚልና የኢንዶኔዥያ ዜግነት ያላቸው ተጠርጣሪዎች በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

የአደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪዎቹ ከብራዚልና ከኢንዶኔዥያ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ ፖሊስ ከሲቪል አቪዬሽን ደህንነት ዋና መምሪያ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሴኩሪቲ፣ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን እና ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር በኤክስሬይ ማሽን በተደረገው ፍተሻ ኮኬይን የተባለ አደገኛ ዕፅ ውጠው ስለተገኙ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እያጣራባቸው እንደሚገኝ ገልጿል።

በአጠቃላይ የብራዚል ዜግነት ካላት ተጠርጣሪ በእንክብል መልክ የተዘጋጀ 2.900 ኪሎ ግራም ኮኬይን የተያዘ ሲሆን እስከአሁን ሰባት ፍሬ ኮኬይን ደግሞ ከሆዷ መውጣቱን የገለፀው ፖሊስ ሌላኛዋ የኢንዶኔዥያ ዜግነት ያላት ተጠርጣሪ ደግሞ 6.70 ኪሎ ግራም በሻንጣ ውስጥ ሰፍታ ፍተሻውን ለማለፍ ስትሞክር ከነ-ኤግዝብቱ በቁጥጥር ሥር መዋሏን አረጋግጧል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥር 28 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply