ኳታር በዶሃ የሚገኘውን የሀማስ ቢሮ ልትዘጋ እንደምትችል ተነገረ።

እስራኤል እና ሀማስን በማደራደር ሚናዋ እየጨመረ የመጣው ኳታር በዶሃ የሚገኘውን የሀማስ የፖለቲካ ቢሮ ልትዘጋ እንደምትችል ሮይተርስ ለኳታር መንግስት ግምገማ ቅርበት ያላቸውን ባለስጣን ጠቅሶ ዘግቧል።

ኳታር፣ የሀማስ የፖለቲካ ቢሮ በዶሃ ስራውን እንዲቀጥል ስለመፍቀድ እና የማደራደር ሚናዋን ስለማቆም ወይም ስላለመቀጠል ጉዳይ ስትገመግም እንደነበር ባለስልጣኑ ተናግረዋል።

ሀገሪቱ ድርድሩ የፖለቲካ ነጥብ ለማስቆጠር በሚጥሩ ፖለቲከኞች ችግር ውስጥ መግባቱን በመግለጽ የቀጥተኛ አደራዳሪነት ሚናዋን እንደምታጤነው ገልጻ ነበር።
ባለስልጣኑ “ኳታር ማደራደሯን ካቆመች፣ የፖለቲካ ቢሮው በመኖሩ የሚያገኙት ነጥብ የለም” ማለታቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

ኳታር የቡድኑን ቢሮ ለመዝጋት ውሳኔ ላይ ከደረሰች ሀማስ ለቆ እንዲወጣ ስመጠየቁ ባለስልጣኑ እንደማያውቁ ተናግረዋል።

ይሁን እንጅ ባለስልጣኑ እንዳሉት የኳታር ውሳኔ እየተካደ ባለው ድርድር ሀማስ እና እስራኤል በሚያሳዩት ተግባር ይወሰናል ብለዋል።

ዋሽንግተን ፖስት አንድ ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ ባለስልጣንን ጠቅሶ አርብ እለት ባወጣው ዘገባ አሜሪካ ቡድኑ ከእስራኤል ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ለመድረስ የሚደረገውን ድርድር ውድቅ ማድረጉን ከቀጠለ፣ ዶሃ ሀማስን እንድታባርረው ነግራታለች።

የሀማስ ተደራዳሪዎች ታጋቾችን እንዲለቀቁ ያስችላል ለተባለ የተኩስ አቁም ድርድር በትናንትናው እለት ካይሮ ገብተው እየተደራደሩ ነው።
በድርድሩ ሀማስ 33 ታጋቾችን ለመልቀቅ ተስማምቷል ተብሏል።

በሔኖክ ወ/ገበርኤል

ሚያዝያ 28 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply