
ፌደራል እና የክልሉ መንግሥት ዝምታን በመረጡበት ጥቃት በወለጋ ዞን ብሔር ተኮር በሆኑ ጥቃቶች ሰላማዊ ሰዎች ሰለባ መሆናቸው መቀጠሉ እየተነገረ ነው። በተለይ በምሥራቅ ወለጋ ዞን ውስጥ በሚገኙት ጊዳ አያና እና ኪራሙ ወረዳዎች ባለፉት ሦስት ቀናት ተባብሰው በቀጠሉት ጥቃቶች በርካቶች ሲገደሉ በመቶ ሺዎች መፈናቀላቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። አሁንም ቀጥሎ እየተካሄደ ስላለው ብሔር ተኮር ግጭት የክልሉም ይሁን የፌደራሉ መንግሥት አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።
Source: Link to the Post