You are currently viewing ወለጋ የደም መሬት =========== ክፍል ሁለት ቀለብ ስዩም 22/10/2014 የአስቆርቱ ይሁዳ የሰው ተክለ ቁመና ያለው የዲያብሎስ የበኩር ልጅ ነበር፡፡ የክርስቶስ ደቀመዝሙር በነበረበት…

ወለጋ የደም መሬት =========== ክፍል ሁለት ቀለብ ስዩም 22/10/2014 የአስቆርቱ ይሁዳ የሰው ተክለ ቁመና ያለው የዲያብሎስ የበኩር ልጅ ነበር፡፡ የክርስቶስ ደቀመዝሙር በነበረበት…

ወለጋ የደም መሬት =========== ክፍል ሁለት ቀለብ ስዩም 22/10/2014 የአስቆርቱ ይሁዳ የሰው ተክለ ቁመና ያለው የዲያብሎስ የበኩር ልጅ ነበር፡፡ የክርስቶስ ደቀመዝሙር በነበረበት ጊዜም የቡድኑ ገንዘብ ያዥ ሆኖ ሰርቷል፡፡ በአንፃራዊነት ሲታይ የአለም መድኒት የሆነውን እየሱስ ክርስቶስን በ30 ብር ለካህናት አለቆች እና አሳለፎ ለመስተት የሚያስችለው ምክንያ የለም፡፡ ነገር ግን ከሀዲ ነበርና አደረገው፡፡ በእዚህም 30 ብር መሬት ተገዛና አኬልዳማ (የደም መሬት) የሚል ስያሜ ተሰጠው፡፡ ይህን እውነት ይዘን ወደ አገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ስንመጣ ወለጋ የደም መሬት ሆና እናገኛታለን፡፡ ብዙዎቻችን እንደምንረዳው በጀርመን ሚሽነሪች ወንጌል መሰበኩን ይሆናል፡፡ ይሁን እንጂ ቆይቶ የተገለፀው እውነት በወለጋ የተሰበከው ወንጌል ሳይሆን ወንጀል ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በተለይም በቄለም ወለጋ የኢትዮጵያና የአማራ-ጠል የአመፅ ሀይላት በእዚያ መፈልፈል ጀመሩ፡፡ ወለጋ-ወለጋ ሆና የተገኘችው በሥራ ወዳዶቹ የአማራ ልጆች ነበር፡፡ እውነት ነው ወለጋ የለማችው በአማራ ልጆች ሀብት፣ እውነትና ጉልበት ቢሆንም ዛሬ ላይ እየተካሄደ ያለው ዘመቻ ግን ወለጋን ከአማራ ልጅ ማጽዳት ሆኖአል፡፡ ይህ ከይሁዳ የማይተናነስ ትልቅ ክህደት ነው ለማለት ይቻላል፡፡ የክህደቱም ውጤት ራሳቸውን ከጥቃት መከላከል በማይችሉ እናቶችና ሕጻናት ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ እናም ወለጋ በአማራ ህዝብ ሕይወት የተገዛች የደም መሬት ሆናለች፡፡ በመጀመሪያ በህወሓት ኢህአዴግ አሁን ደግሞ በኦህዴድ ብልፅግና ቅድመ እውቅና እንዳለው የሚነገርለት ኢትዮጵያን የመበታተን ስውር አጀንዳ በሁሉም አቅጣጫ አማራን ከያለበት በማጥፋት ላይ አተኩሮአል፡፡ ሕወሓት፦ “ትግራይ እስክትለማ – ኢትዮጵያ እናድማ!” የሚል መርህ አንግቦ ለ27 አመታት እንዳደረገው ሁሉ አሁን ደግሞ ተረኛው የኦህዴድ ብልፅግና ሆኖአል፡፡ አዎ! የኦህዴድ ብልፅግና ኢትዮጵያን በየአቅጣጫው እያደማ – ኦሮሚያን ማልማት ሆኖአል ተግባሩ፡፡ የኦህዴድ ብልፅግና ከተቻለ ለሚቀጥሉት ሰላሳና አርባ አመታት ኢትዮጵያን የመግዛት ፍላጎት አለው፡፡ ካልተቻም ኦሮሚያን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል በኦነግ ሸኔ አማካኝነት እንደሚጠቀም ከወዲሁ የሚተነብዩ አንዳንድ ወገኖች አልታጡም፡፡ ሁሉም ሰው እንደሚያውቀው ወደየትኛውም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ብንሄድ የአማራ ተወላጆች በብዛት ይገኛሉ፡፡ በኦሮሚያ ምድር ብቻ ከ10 እስከ 15 ሚሊዮን የሚገመቱ የአማራ ተወላጆች እንዳሉ ነው የሚነገረው፡፡ በእዚያ ላይ ጉራጌውን፣ ሲዳማውን፣ ሀዲያውን፣ ወላይታውን፣ ትግሬውንና ሌላውንም ደምሩበት፡፡ ታዲያ ይህን ያህል በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምነውን ህዝብ በጉያው ይዞ ኦሮሞ ወዴት ሊገነጠል ይችላል!? እውነታው ጨርሶ የማይቻልና የማይሞከር ቢሆንም ብዙ የሕዝብ ቁጥር ያለውን የአማራን ተወላጅ የማስወገድ ዘመቻ በወለጋ ተጀምሯአል፡፡ የታሪክ ድርሳናት እንደሚስረዱት የኦሮሞ ነገድ ከ400 አመታት በፊት የነበረው ይዞታ በቦረና እና መዳወላቡ የተወሰነ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የአማራ ህዝብ በግራኝ አህመድ ወረራ በመዳከሙ የኦሮሞ ህዝብ ያንን ተከትሎ የግዛት መስፋፋት አደረገ፡፡ ከእዚያ በኋዋላም ከሁሉም የኢትዮጵያ ነጋዶች ጋር በጋብቻና አብሮ በመኖር መርህ ተሳስሮ፣ ተዋልዶና፣ ተጋምዶ በመኖር ላይ ቢሆንም አንዳንድ ልጆቹ የግብፅና የምዕራባውያን ሴራ አራማጆች ሆነው በተለይም አማራን በማስወገድ ሴራ ላይ ተጠምደዋል፡፡ ሊሆን የማይችል ሴራ . . . . . እንደታሰበው ኢትዮጵያን መበታተን ቢችሉ እንኳ ኦሮሚያ ለአንዲት ቀን አይደለም ለአንድ ሰአት እንኳን ኦሮሚያ ለአንዲት ሰአት እንኳን በሰላም ለመኖር እድሉ የላትም፡፡ ምክንያቱም ኦሮሚያ ከትግራይ፣ ኦሮሚያ ከአፋር፣ ኦሮሚያ ከአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ከሶማሊያ፣ ኦሮሚያ ከደቡብ ሕዝቦች፣ ኦሮሚያ ከከፋ፣ ኦሮሚያ ከጋምቤላ፣ ኦሮሚያ ከቤንሻንጉል ክልል ጋር የመሬት ይገባኛል ውዝግብ ስላለ ይሆናል፡፡ እናም ከማንም በላይ የኢትዮጵያ አንድነት የሚጠቅመው ለኦሮሞ ሕዝቦች እንደሆነ በውል ለይተው ሊያውቁት ይገባል፡፡ ወለጋ ሆይ! በአማራ ላይ የፈፀምሽውን የዘር ማጥፋት እልቂት ብረሳ ቀኜ ትርሳኝ! ============================== አንዳንዶች “የጊዜ እንጅ የሰው ብርቱ የለም” ይላሉ፤ ሌሎች እንዲሁም “ቀን የሰጠው .. ቅል፣ ቀን የጣለውን ድንጋይ ይሰብረዋል” ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ በመላው ወለጋ በአማራ ተወላጅ ላይ የተፈጸመው ግድያና ማፈናቀል ከእዚህ ሁለት ድምዳሜዎች የወጣ አይደለም፡፡ ሊሆንም አይችልም፡፡ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሮጠው ማምለጥ የማይችሉ እናቶችና ህጻናት፣ አገር ሰላም ነው፣ ህግ አስከባሪ የክልልና የፌዴሬራል መንግሥታት አሉ ብለው ተዘናግተው በመቀመጣቸው ደም በጠማቸው የኦሮሞ ሀይሎች በጅምላ ተረሸኑ፣ ሆዳቸው በሳንጃ ተቀደደ፣ አንገታቸውም እንደ ፋሲካ በግ በካራ ታረደ፣ በገጀራም ተቀላ፡፡ በታሪክ በሰው ልጆች ላይ ያልተፈጸም ግፍና እልቂት በአማራ ተወላጆች ላይ ደረሰ፡፡ በብዙ ሽዎች የሚቆጠሩ የአማራ እናቶችና ህጻናት ለሰኔዋ እቴቴ ጭዳ ሆኑ፡፡ የአማራና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንቶችም በሚዲያ የይስሙላ ውግዘት አስተላለፉ፡፡ በምፀት፡፡ የፌዴራሉ መንግስትማ የንፁሃን አሰቃቂ ግድያ ስሜት የሰጠው አይመስልም፡፡ አሁንም ቢሆን ከሞት የተረፉት አማራዎች በከፍተኛ ጭንቀትና ብሶት እያሰሙ ይገኛሉ፡፡ እናም ወለጋ ሆይ! በአማራ ላይ የፈፀምሽው የዘር ማጥፋት እልቂት እንዴት ይረሳል!? በተፈፀመው አስነዋሪ ግድያ በበኩሌ እኔም እናት ነኝና ነፍስያዬ በውስጤ ቀልጣለች፣ አንጀነቴ በሀዘንና ትካዜ ተኮማትራል፣ ልቤ ክፉኛ ደምቷል፣ አእምሮዬም ተቃውሶል፡፡ በሀገርና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም በሀዘን ባዘኑ፡፡ ራሄል ስለ ልጆቿ ካለቀሰችው በላይ አልቅሰዋል፡፡ መጽናናትም የለም፡፡ እነሆ ጠዋት ማታ የቆሰልነው ቁስል እየቆጠቆጠን የተፈፀመውን እልቂት እንዳንረሳ ሆነናል፡፡ ወደፊትም የሚረሳ አይደለም፡፡ አዎ! ጠባሳው በመላ አካላችን ታትሟል፡፡ ጠባሳውን ባየን ቁጥጥር ህመማችን ይቀሰቀሳል፡፡ ወለጋ ሆይ! በአማራ ላይ የፈጸምሽውን የዘር ማጥፋት እልቂት ብረሳ ቀኜ ትርሳኝ!! እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያውያንን ይጠብቅ፡፡ አሜን። ትግሉ ይቀጥላል!! ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!! © ቀለብ ስዩም #በቃ! #እምቢ! #AmharaGenocide! ሰ.አሜሪካ:- ሰኔ 22/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply