ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የምግብ በጀት ሙሉለሙሉ አልቆብኛል ማለቱ ተሰምቷል፡፡ጣብያችን ኢትዮ ኤፍ ኤም ከተማሪዎች እና ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ባገኘችው መረጃ መሰረት ዩኒቨርሲቲው…

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የምግብ በጀት ሙሉለሙሉ አልቆብኛል ማለቱ ተሰምቷል፡፡

ጣብያችን ኢትዮ ኤፍ ኤም ከተማሪዎች እና ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ባገኘችው መረጃ መሰረት ዩኒቨርሲቲው የምግብ በጀቱን መጨረሱን ገልፃል፡፡

ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በተላከልን የፎቶ ማስረጃዎች ዩኒቨርሲቲው ለተማሪዎች የሚያቀርበውን የምግብ አገልግሎት ማስቀጠል እንደከበደው ይጠቅሳ፡፡

በዚህ የበጀት እጥረት ምክንያት ዩኒቨርሲቲው ከቀን 11/08/2016 ዓ/ም ጀምሮ የምግብ ሜኑ ማስተካከያ ለማድረግ መገደዱን እንዲሁ ጣብያችን ለመረዳት ችሏል፡፡

የተማረዎች የምግብ በጀት ሙሉ በሙሉ ከተጠናቀቀ ወራትን አስቆጥሯል የሚለው የዩኒቨርሲቲው ማስታወቂያ በነበረው አካሄድ መሰረት መቀጠል አልቻለኩም ማለቱን ተመልክተናል፡፡

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ጣብያችን ኢትዮ ኤፍ ኤም ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እና ተማሪዎችን ለማነጋር ሞክሯል፡፡

ያለው ሁኔታ እጅግ ከባድ ሆኖብናል ያሉን ከጣቢያችን ጋር ቆይታ የነበራቸው ተማሪዎች ከበጀት እጥረቱም በፊት በዩኒቨርሲቲው የሚቀርበው ምግብ ጥራቱን ያላሟላ ነው መሆኑን ነግረዉናል።

ባለው ሁኔታ የተነሳ ከ ምግብ ውጪ ስለ ትምህርት እንዳናስብ ጭምር ሆነናል የዩኒቨርሲቲው ተማሪም ዳቦ በሻይ እየበላ መማር እንዳማረረው አንስተዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደምም በመብራት እና በተለያየ ምክንያት በተደጋጋሚ ምግብ ለማቅረብ ሲቸገር መቆየቱ እንዲሁ ተማሪዎቹ ያነሳሉ፡፡

ሌላው ከጣብያችን ጋር ቆይታ ያደረገ ተማሪ በምግቡ ሁኔታ ክፉኛ መማረሩን ያነሳ ሲሆን ችግሩ እንዲፈታ በተደጋሚ ጠእያቄው ቢነሳም በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ እንደ ፀብ አጫሪ የመቆጠር ሁኔታ አለ ብሏል፡፡

ሌላው መመገቢያው ሰዓት ትንሽ አረፈድ ተደርጎ ከተደረሰ ምግቡ በፍጥነት ስለሚያልቅ ደረቅ እንጀራ ብቻ ተቀብለን የምንወጣበት ቀን ብዙ ነው ብለውናል፡፡

በቅሬታ መልክ ይሰማ የነበረው የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ጥራት እና መቆራጥ ከሰሞኑ ዩኒቨርሲቲው ከአቅሙ በላይ መድረሱን ለተማሪዎች በለጠፈው ማስታወቂያ ገልፃል፡፡

ይህንን በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጡን ጣብያችን ወደ ዩኒቨርሲቲው ደውሎ ምላሽ ለማግኘት ሞክሯል።

ይሁን እንጂ ጣብያችን ያናገራቸው ዩኒቨርሲቲው ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ስለተባለው ጉዳይ ምንም መረጃ እንደሌላቸው ነግረውናል።

በአቤል ደጀኔ

ሚያዝያ 14 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply