ወላይታ ዲቻ ዋና አስልጣኙን  ደለለኝ ደቻሳን አሰናበተ

ወላይታ ዲቻ ዋና አስልጣኙን ደለለኝ ደቻሳን አሰናበተ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ወላይታ ዲቻ ስፖርት ክለብ ዋና አስልጣኝ ደለለኝ ደቻሳ እና ምክትል አሰልጣኙን ማሰናበቱን አስታወቀ፡፡
 
የወላይታ ዲቻ የስፖርት ክለብ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሳሙኤል ፎላ በክለቡ ወቅታዊ አቋም ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።
 
አቶ ሳሙኤል ከስድስት ጨዋታዎች አንድ ብቻ በማሸነፉ በዋና እና በምክትል አሰልጣኝ እንድሁም ስራ አስከያጁ መሰናበታቸውን ገልጸዋል።
 
የወላይታ ዲቻ ስፖርት ክለብ ህዝባዊ ክለብ በመሆኑ ከወላይታ ህዝብ ህልውና ጋር የተያያዘ ነው ብለዋል።
 
ከፋይናንስ ምንጭ ጋር ተያይዘው ተጨማሪ ምንጭ የማመንጨት ስራ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
 
በአጭር ቀናት ውስጥ የአስልጣኝ ቅጥር እንዲፈጽም ክለቡ ማስታወቂያ ማውጣቱም ተገልጿል።
 
በአጠቃላይ 123 ሰራተኞች ያሉት ዲቻ ክለብ ዓመታዊ ወጪ 62 ሚልየን ብር እንደደረሰም ነው የጠቀሱት።
 
በማቴዎስ ፈለቀ
 
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 

The post ወላይታ ዲቻ ዋና አስልጣኙን ደለለኝ ደቻሳን አሰናበተ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply