ወልቂጤ አራት ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ

https://gdb.voanews.com/01000000-0aff-0242-758a-08db1053da4a_tv_w800_h450.jpg

ፖሊስ የሞቱት ሰዎች ሦስት ናቸው ብሏል

በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ከክልሉ የፀጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት አራት ሰዎች መገደላቸውንና 17 መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ።

በአካባቢው ለአንድ ዓመት ያህል የመጠጥ ውሃ በመቋረጡ አቤቱታ ለማሰማት አደባባይ መውጣታቸውን አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የሰጡ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ስፔሻላይዝድ ሪፌራል ሆስፒታል ቆስለው ወደ ሆስፒታሉ ከመጡ 16 ሰዎች ውስጥ ሁለቱ ወዲያውኑ ሲሞቱ ሁለቱ ከፍ ላለ ሕክምና ወደ አዲስ አበባ መላካቸውን ገልጿል።

የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በከተማው በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ሁከት መፈጠሩን ገልፀው የሞቱት ሰዎች ሦስት መሆናቸውና ስምንት መቁሰላቸውን አስታውቋል።

ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply