You are currently viewing ወልቂጤ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴዋ ተመልሳለች።

ወልቂጤ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴዋ ተመልሳለች።

ለአንድ ሳምንት ዝግ ሆና የሰነበተችው ወልቂጤ ከተማ ዛሬ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴዋ ተመልሳለች።
የወልቂጤ ከተማ ማህበረሰብ ተደጋጋሚ በከተማው የሚስተዋለውን የውሀ እጥረት እንዲቀረፍለት ሲጠይቅ መቆየቱ ይታወሳል።

የውሀ ችግሩ እንዲፈታለት ጥያቄውን በማቅረብ ላይ ሳለ በተፈጠረ ግጭት የዜጎች ህወት ማለፉም አይዘነጋም፡፡
ይህንንም ተከትሎ ዜጎች ከቤት ያለመውጣት አድማ አድርገው ለአንድ ሳምንት ያህል ቆይተዋል፡፡

በዛሬው እለት በወልቂጤ ከተማ እና አካባቢ መደበኛ እንቅስቃሴ መኖሩን የዞኑ እንዲሁም የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
በዚህም አንዳንድ ምግብ ቤቶች፣ ፋርማሲ ቤቶች እና የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቆች ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ መመለሳቸውን ነግረውናል፡፡
በትናንትናው ዕለት ከሽማግሌዎች፣ ጉዳት ከደረሰባቸው ቤተሰቦችና ወጣቶች ጋር በመወያየት ዛሬ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴዋ እንደተመለሰች የከተማዋ ነዋሪዎች ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
የካቲት 15 ቀን 2015 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply