#ወልቃይት !! በወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ጉዳይ መንግስት የያዘው አካሄድ ግልጽ ባለመሆኑ ስጋት ገብቶናል ሲሉ የወልቃይት ወረዳ አስተዳዳሪ ገለጹ። ታሕሳስ 20 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ…

#ወልቃይት !! በወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ጉዳይ መንግስት የያዘው አካሄድ ግልጽ ባለመሆኑ ስጋት ገብቶናል ሲሉ የወልቃይት ወረዳ አስተዳዳሪ ገለጹ። ታሕሳስ 20 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ አስተዳዳሪው አቶ ክብረአብ ስማቸው እንደገለጹት በፌደራሉ መንግስት በኩል ወልቃይትን በተመለከተ የተያዘው አቋም ግልጽ አይደለም፡ በዚህም ስጋት ገብቶናል ብለዋል። ህወሀት በአንዳንድ ቦታዎች ትንኮሳ መጀመሩን የገለጹት አቶ ክብረአብ ለሰላም ሂደቱ ስንል የአጸፋ እርምጃ ከመውሰድ ተቆጥበናል ሲሉ ተናግረዋል። ላለፉት ሁለት ዓመታት በጀት የተነፈገው የወልቃይት አከባቢ በከፍተኛ ችግር ውስጥ መውደቁንም ገልጸዋል። በጦርነቱ እኛም ተጎድተን፡ የመሰረተ ልማት አውታሮች ፈራርሰውብን፡ እርዳታው ግን የሚጎርፈው ወደ ትግራይ ብቻ ነው ሲሉም ቅሬታቸውን ገልጸዋል። ቢሆንም በደም በአጥንት የተገኘውን ነጻነት አሳልፈን የምንሰጠው አይደለም ብለዋል የወልቃይት ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ክብረአብ ስማቸው። ዘገባውን ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን አንከር ሚዲያ በተባለ ዩትዩብ በየነ መረብ ዘግቧል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply