You are currently viewing ወልቃይት – ኢትዮጵያን የማዳን የመጨረሻ ጥሪ‼️  ******************************* ተስፋፊውና ፋሽስቱ የትግራይ ወራሪ ሃይል የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላትን በጭካኔ ከ…

ወልቃይት – ኢትዮጵያን የማዳን የመጨረሻ ጥሪ‼️ ******************************* ተስፋፊውና ፋሽስቱ የትግራይ ወራሪ ሃይል የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላትን በጭካኔ ከ…

ወልቃይት – ኢትዮጵያን የማዳን የመጨረሻ ጥሪ‼️ ******************************* ተስፋፊውና ፋሽስቱ የትግራይ ወራሪ ሃይል የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላትን በጭካኔ ከጨፈጨፈበት ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ጀምሮ በማይካድራ፣ በአፋር፣ በወሎ፣ በሸዋና፣ በጎንደር ልዩ ልዩ ቦታዎች የሚኖሩ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የግፍ ጭፍጨፋ ፈፅሟል፤ እናቶቻችንና እህቶቻችን በቡድን ደፍሯል፤ የህዝብ መገልገያ ተቋማትን ሙሉ ለሙሉ አውድሟል፤ የግለሰቦችንና የመንግስት ንብረት ዘርፏል፤ መሰረተ ልማቶችንና የእምነት ተቋማትን አውድሟል፤ በአጠቃላይ በህዝባችን ላይ “ይህ-ቀረሽ” የማይባል ሰቆቃና ግፍ ፈፅሟል። ባንዳው ትህነግ/ወያኔ ከፍጥረቱ ጀምሮ የተጣባውን ኢትዮጵያን የመበታተን፣ ህዝቧን የማጫረስና፣ በተለይም የአማራን ህዝብ የማጥፋት እኩይ አላማ ለማሳካት ያልቧጠጠው መሬት የለም። ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ ቆራጥና ጀግና ልጆች ብርቱ ክንድ ከተደቆሰና እንዳይድን ሆኖ ከቆሰለ በኃላም ቢሆን የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመና የህዝብ ደም በከንቱ ለማፍሰስ እየተቅበዘበዘ የሚገኝ ሲሆን፤ ዳግም ኢትዮጵያን ለመውረርና በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በጠለምት፣ በራያና፣ በአፋር ግንባሮች መጠነ ሰፊ ጦርነት ለመጀመር ዝግጅቱን አጠናቋል። ይህ የጠላት አስከፊ የወረራና የእልቂት ዘመቻ በህዝባችን ላይ ሊፈፀም ጫፍ በደረሰበትና ኢትዮጵያውያን በሙሉ ተረባርበን ሀገራችን ለማዳን ወደ ጦር ግንባር መዝመት በሚገባን በዚህ ቀውጢ ሰአት የአማራ ልዩ ሃይል፣ ሚሊሻና፣ ፋኖ ከወልቃይት፣ ጠገዴና፣ ጠለምት ወጥቶ ወደ ቀሪው የጎንደር ክፍልና የጎጃም አካባቢዎች አንዲዛወር መወሰኑ በእጅጉ አስደንግጦናል። በወልቃይት ግንባር በህዝባዊ ማዕበልና በተለያዩ አቅጣጫዎች የሚመጣውን የጠላት ሃይል በሀገር መከላከያ ሰራዊት ብቻ ለመሸፈን የተደረሰበት ውሳኔ ጠላት ከዚህ ቀደም በወሎ፣ በሸዋ፣ በአፋርና፣ በጎንደር የተለያዩ አካባቢዎች የተቀዳጃቸውን ጊዚያዊ ድሎችና በህዝባችን ላይ የፈፀማቸውን ግፍና መከራዎች በወልቃይት፣ በጠገዴና፣ በጠለምት የአማራ ህዝብ ላይ እንዲደገሙና “ለዳግማዊ ማይካድራ” እልቂት መደላድል የሚፈጥር ታሪካዊ ስህተት ነው ብሎ ድርጅታችን በፅኑ ያምናል። ይልቁንም ወልቃይትና አካባቢውን በትግራይ ወራሪ ሃይል ዳግም በወረራ አስይዞ የኢትዮጵያ መንግስትን ከትህነግ/ወያኔ ጋር ለድርድር ለማስቀመጥ የተጠነሰሰው ሴራ ኢትዮጵያንም እንደ ሃገር ህልውናዋን አደጋ ላይ የሚጥልና ሉዓላዊነቷን የሚያጠፋ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ሁኔታ የአማራን ህዝብ ለእልቂት የሚዳርግና በሀገራችን ውስጥ የማያባራ የእርስ በእርስ ግጭትና ጦርነት ውስጥ የሚዘፍቀን በመሆኑ የአማራ ልዩ ሃይል፣ ሚሊሻና፣ ፋኖ ከወልቃይትና አካባቢው እንዲነሳና በመከላከያ ሰራዊት ብቻ እንዲሸፈን የተደረሰበትን ውሳኔና ስምምነትን ድርጅታችን ልሳነ ግፉዓን አጥብቆ ይቃወማል። ስለሆነም፦ 1ኛ. ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያን ለታላቅ ድል ያበቃውንና ህብረ-ብሔራዊ አንድነታችንን ያጠናከረውን በአንድነት ጠላትን ገጥመን በጋራ ድልን የተቀዳጀንበትን “የኢትዮጵያ ጥምር ሃይል” ህብረት ተጠናክሮ እንዲቀጥልና የአማራ ልዩ ሃይል፣ ሚኒሻና፣ ፋኖ ከወልቃይትና አካባቢው አንዳይነሳብን በህዝባችን ስም አጥብቀን እንጠይቃለን! 2ኛ. ትህነግ/ወያኔ የመጨረሻውን የሞት ሽረት ጦርነት ለማድረግና ወልቃይትን ይዞ ለመደራደርና ብሎም ሀገር ለመገንጠል የመጨረሻው ዝግጅቱን ጨርሶ የሁኔታዎችን ምቹነት እየተጠባበቀ ይገኛል። ስለሆነም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከሀገር መከላከያ ሰራዊታችን፣ ከአማራ ልዩ ሃይል፣ ሚሊሻ፣ ፋኖ እንዲሁም ከሁሉም አደረጃጀቶች ጎን በመቆም የጠላትን የመጨረሻ ወረራ ዳግም በአንድነት እንድንመክት በህዝባችን ስም ሀገር የማዳን ጥሪያችን እናስተላልፋልን! 3ኛ. የአማራ ህዝብ ሆይ! የቀበርከው ጠላትህ የትግሬ ወራሪ ሃይል ከሞት ተነስቶ ዳግም ሊወርህና ሚስትህንና ሴት ልጅህን ከፊትህ ላይ ሊደፍር፣ የአባቶችህን ርስትህ ሊወስድ፣ ሀገርህ ኢትዮጵያን ሊያፈርስ እየገሰገሰ ነው። ስለዚህ ሴት-ወንድ፣ ዛሬ-ነገ፣ ጨርቄን-ማቄን ሳትል እራስህን እንድታዘጋጅና ለኢትዮጵያ ጥምር ሃይል አኩሪ ደጀንነትህን አጠናክረህ እንድትቀጥል ልሳነ ግፉዓን ድርጅት አጥብቆ ያሳስባል! 4ኛ. የትግራይ ወራሪ ሃይል ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ሀገራችንና በመላው ህዝባችን ላይ በከፈተው የጭካኔ ወረራና በፈፀመው ጭፍጨፋ ከጎናችን በመቆምና ክቡር መስዋዕትነት በመክፈል ህዝባች ከእልቂትና ሀገራችን ከመፍረስ ለታደጋችሁ ወገኖቻችን በሙሉ ላደረጋችሁት ታሪካዊ አጋርነት እያመሰገን፤ ዛሬም እንደ ትላንቱ ከጎናችን በመቆም በዘመናት ሂደት ውስጥ ያልተናወጠውንና ያልተዛነፈውን አጋርነታችሁንና ወገናዊነታችሁን ታረጋግጡ ዘንድ በወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት ህዝብ ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን! 5ኛ. በመጨረሻም በመላው ዓለም የምትገኙ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን! መላው የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች! የኢትዮጵያ ወዳጆች! ጠላታችን የትግሬ ወራሪ ሃይል በህዝባችን ላይ የጀምላ ፍጅት ለመፈፀምና ኢትዮጵያችን ለማፍረስ ቆርጦ ተነስቷል። ስለሆነም ማንኛውንም ጥቃቅን ልዩነቶች ወደ ጎን በመተው በምትችሉትና በማንኛውም መንገድ ከህዝባችንና ከሀገራችን ጎን በመቆም ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ግዴታችሁን ትወጡ ዘንድ በህዝባችንና በኢትዮጵያ ስም ጥሪ እናቀርባለን! ድል ለኢትዮጵያ ጥምር ሃይል! ልሳነ ግፉዓን ድርጅት ሚያዝያ 29 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply