ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን መቀበል ጀመረ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 5፣2014 ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን መቀበል ጀመረ :: በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ከፍተኛ ውድመት ተፈፅሞበት ተዘግቶ የቆየው የወልድያ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ተማሪዎቹን መቀበል ጀምሯል። የዩኒቨርሲቲው ጥበቃና ደህንነት ሰራተኞች አስፈላጊውን የፍተሻ ስራ እያከናወኑ ጥሪ የተደረገላቸው
ተማሪዎች ከዛሬ ጠዋት ጀምረው ወደ ግቢ በመግባት ላይ ናቸው፡፡ ዩኒቨርሲቲው መጋቢት 5 እና 6 ቀን 2014 ዓ.ም ለተማሪዎቹ ምዝገባ የሚያካሂድ ሲሆን÷
ለተማሪዎቹም የትራንስፖርት አገልግሎት ማመቻቸቱን አስታውቋል። በዚሁ መሠረት ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በወልዲያ መናኸሪያ፣ በፒያሳ፣ በአዳጎና ጎንደር በር ፌርማታዎች ላይ በመገኘት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply