You are currently viewing #ወልድያ‼… ባለኝ ተግባቦት የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ለሁሉ ባለድርሻ አካላት በስልክና በአካል አስረድቻለሁ። የገጠመንን ፈተና በገለልተኝነት አስረድቻለሁ። በዚያም መሰረት ለዞን ፀጥታዎች…

#ወልድያ‼… ባለኝ ተግባቦት የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ለሁሉ ባለድርሻ አካላት በስልክና በአካል አስረድቻለሁ። የገጠመንን ፈተና በገለልተኝነት አስረድቻለሁ። በዚያም መሰረት ለዞን ፀጥታዎች…

#ወልድያ‼… ባለኝ ተግባቦት የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ለሁሉ ባለድርሻ አካላት በስልክና በአካል አስረድቻለሁ። የገጠመንን ፈተና በገለልተኝነት አስረድቻለሁ። በዚያም መሰረት ለዞን ፀጥታዎች ፋኖዎች ጋር ነገሩ በንግግር እንድፈታ የፋኖ አመራሮችና የዞን ፀጥታዎች ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በግንባር ተገናኝተው የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት እየተወያዩ ነበር። በመጀመሪያ የምስራቅ አማራ ፋኖ መሪ ፋኖ ምሬ ዎዳጆ ጋር የነበረው ችግር ተፈትቶ መንገድ እንደጀመረ፤ ሮቢት ላይ ተኩስ በመከፈቱ ምክንያት ነገሮች መልሰው ቢወጣጠሩም፤ ፋኖ ምሬ መለቀቁ ሲታዎቅ ነገሮች ረግበው፤ ምሬም ወደ ቆቦ ጉዞውን ቀጠለ። ወልድያ ያለው ድባብ ዝም ያለ ሲሆን የተዘጉ መንገዶችን ለማስከፈት መከላከያ ሰራዊቱ ከመነኻሪያ ጀምሮ ያለውን የተዘጋውን ድንጋይና እንጨት እያስነሳ በደብ_ረገሊላ (ፒያሳ) ዞሮ ወደ አዳጎ አቅጣጫ መጣ፤ በዚህ ጊዜ እኔ አደጎ አደባባይን አልፌ ወደ አዳራሹ አቅጣጫ እንደደረስኩ ሩምታ ተኩስ ተከፈተ። ለመከላከያ፦ በዚህ ልክ ከፋኖ ጋር እልህ መጋባት አያስፈልግም ነበር። እኛ ባለንበት ከተማ ለሰላም ውይይት ፋኖ ይሁንታውን ሳይከለክል! ለምን??? የወልድያና የራያ ህዝብ አጠቃላይ የሰሜን ወሎ ህዝብ ጥቅምት24ትን ቁጭት ይዞ ነው… የበለጠ ወያኔን ለመፋለም ፋኖ የሆነው!!! መከላከያ ቢያውቅ ፋኖ ጥቃት መላሹ እንጅ ባላንጣው አይደለም። ህዝቡ ሰኔ24 ቀን2013ዓ/ም መከላከያው «ወደ ደጀን ህዝቤ ገባሁ» ሲል በእልልታ በፍቅር በአንድነት ነበር የተቀበለው። እኔን ጨምሮ መከላከያ በወያኔ ቡድን የተደረገበትን ክደት እንደ እግር እሳት ያንገበግበኛል!!! በህልውና ዘመቻው መከላከያው ቢራብ አልብልቶ! ቢጠማ አጠጥቶ! ቢታረዝ አልብሶ! ቢሰዋ በክብር ቀብሮ! አርባ ፍትሃት! አውጥቶ! በብዙ ነገር ከመከላከያው ጎን ቆሞ!!! እውነት ነው ህይወቱን ለሚሰጥ አካል መስተንግዶ ሲያንስ ነው!!! ነገር ግን እንደ ወያኔ ክህደት እንደ ትግራይ ህዝብ ድርጊት ይህ ህዝብ ውለታው ይሄ አልነበረም። አምናለሁ ውጊያ ላይ የነበረ ሰው የፋኖና የመከላከያን መናበብ የሚያውቀው ያውቀዋል በተለይ እኔ በነበርኩበት ግንባሮች፤ ከሰሜን እዝ ሃያ ሶስተኛ! ከደቡብ እዝ ሃያ አንደኛ! የምስራቅ እዝ! እንድሁም ልዩ ዘመቻና ኮማንዶ ብርጌዶች ክፍለ ጦሮች የፋኖን ውመታና መናበብ ያውቁታል!!! መታወቅ ያለበት! ፋኖ ሆኖ ችግር የለበት ማለቴ አይደለም። ይሄን የፋኖም አመራሮች ያውቃሉ በድስፕሊን እየታየ ያለ ጉዳይ ነው። በዚያው ልክ መከላከያውም ውስጥ በተመሳሳይ አለ… መከላከያው ካለበት ኃላፊነት አንፃር ነገሮችን በእርጋታ መሄድ አለበት። ዛሬ የተከፈለው ዋጋ ይበቃል! ከተማችን በጥላት ተኩስ ያልተከፈተባት አሁን የኛ ወገን በምንለው ኃይል እንድህ አይነት የተኩስ ልውውጥ መደረጉ ያሳዝናል!!! አሁንም መከላከያው ነገሮችን በእርጋታ ቢመራቸው የተሻለ ነው። ጥላት በቆቦ ወረዳ በስድስት ኪሎሜትር ተቀምጦ በራስ ወገን ላይ ይሄን ያክል ተኩስ ተገቢ አይደለም። የሰሜን ወሎ አመራሮችም ህዝባችሁን በአግባቡ ምሩ!!! የህዝቡ ፍላጎት ይታወቃል! እኔ በማውቀው ልክ ይህ ህዝብ ከእናንተ ጥርጣሬና ፍርሃት! ስጋት በስተቀር ጥላቱን ያውቃል! ይህ ህዝብ ትላት በጥላት እጅ እንኳን ተይዞ የዚህን ያክል በሩምታ ተኩስ አልተሸማቀቀም! ከመራችሁ ከሁሉም ነገር ፊት ቅደሙና ምሩት!!! አልበዛም እንደ!??? የጥላትም ጦር ሲመጣ ፈርታችሁ!!! የወገንም ጦር ሲመጣ ፈርታችሁ!!! አይሆንም! ተው ማለት ልመዱ!!! አበቃሁ!!! ለህዝቡ ግን የማስተላልፈው ሰከን ብሎ ነገሮችን እንዲያይ ብቻ ነው! ትዕግስት ፍሬ አላት!!! ከተደማመጥን እናሸንፋለን!!! በቴዎድሮስ አያሌው (ሀብታሙ) ሚያዚያ፪ ቀን፳፻፲፬ዓ/ም ተጣፈ። 02/08/2014ዓ/ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply