ወሎ ቤተ አማራ ማህበር ለሁለተኛ ጊዜ በራያ ቆቦ እና ወረባቦ ለሚገኙ አርሶ አደሮች የ500,000ብር (አምስት መቶ ሽህ ብር) ግምት ያለው ድጋፍ አደረጉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

ወሎ ቤተ አማራ ማህበር ለሁለተኛ ጊዜ በራያ ቆቦ እና ወረባቦ ለሚገኙ አርሶ አደሮች የ500,000ብር (አምስት መቶ ሽህ ብር) ግምት ያለው ድጋፍ አደረጉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 12 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የወሎ ቤተ አማራ ማህበር አስተባባሪ ወጣት ፍሰሃ መለሰ ለአሻራ ሚዲያ በስልክ እንደገለጹት በ2013 ዓ.ም የመኸር ምርት ዘመን በሰሜን ወሎ ዞን በሚገኙ ወረዳዎች ላይ ሰብላቸው በአንበጣ መንጋ ለወደመባቸው አርሶ አደሮች ድጋፍ ለማድረግ በማህበሩ ስም የባንክ ሂሳብ በመክፈት ባሰባሰብነው 500. 000 ( አምስት መቶ ብር ) ገንዘብ ድጋፍ አድርገናል ብለዋል፡፡ ድጋፉን ያደረጉት በወረባቦ እና ራያ ቆቦ ለሚገኙ እና ለተመረጡ አርሶ አደሮች ሲሆን ለእያንዳንዳቸው አንድ አንድ ሊትር ዘይት እና ዱቄት የተሰጣቸው ሲሆን በዚህም 600( ስድስት መቶ) ሊትር ዘይት ፤ 150(አንድ መቶ ሀምሳ ) ኩንታል ዱቄት እና 80 ( ሰማኒያ) ደርዘን ደብተርን ጨምሮ በሁለቱም ወረዳዎች ለሚገኙ አርሶ አደሮች ማጨጃ የሚሆን ለእያንዳንዳቸው ሰላሳ ስምንት ማጭድ ድጋፍ ማድረጋቸውን የማህበሩ አስተባባሪ ገልጸዋል፡፡ በዘንድሮው ዓመት በሰሜን እና ደቡብ ወሎ በሚገኙ ወረዳዎች የአንበጣ መንጋ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ በመሆኑ እርዳታውን ለመሰብሰብ እንዳነሳሳቸው ገልጸው ልክ እንደ ወሎ ቤተ አማራ ማህበር ሁሉ ሌሎችም በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ወገኖች ድጋፍ ያደርጉ ዘንድ የወሎ ቤተ አማራ ማህበር አስተባባሪ ወጣት ፍሰሃ መለሰ ጥሪ አቅርበዋል ሲል አሻራ ሚዲያ ነው የዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply